በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

አርዓያ የሚሆኑ ሰዎች—ሙሴ

አርዓያ የሚሆኑ ሰዎች—ሙሴ

አርዓያ የሚሆኑ ሰዎች—ሙሴ

ሙሴ ጥሩ የሚባል ሕይወት ለመምራት የሚያስችሉ አጋጣሚዎች ነበሩት። ሙሴ ያደገው በፈርዖን ቤተ መንግሥት ሲሆን የግብፃውያንን ጥበብ ሁሉ ተምሮ ነበር። (የሐዋርያት ሥራ 7:22) ታዲያ ይህን ሥልጠና እንዴት ይጠቀምበት ይሆን? ሙሴ በቀሰመው ትምህርት ተጠቅሞ ዝና ማትረፍ፣ ሀብት ማካበት እንዲሁም ሥልጣን ማግኘት ይችል ነበር። እሱ ግን እነዚህን ነገሮች በማሳደድ ላይ አላተኮረም፤ በእኩዮች ተጽዕኖም አልተሸነፈም። ሙሴ ያደረገው ምርጫ ብዙዎችን የሚያስገርም ነው። “ከአምላክ ሕዝብ ጋር መንገላታትን” መርጧል። (ዕብራውያን 11:25) ሙሴ እንዲህ ያለ ምርጫ በማድረጉ የቀረበት ነገር አለ? በፍጹም። አምላክን ለማገልገል እና ሰዎችን ለመርዳት በመምረጡ አስደሳችና የሚያረካ ሕይወት መምራት ችሏል።

አንተም ጥሩ ትምህርት የማግኘት አጋጣሚ ካለህ የቀሰምከውን እውቀት የምትጠቀምበት እንዴት ነው? እውቀትህን ሀብት ለማካበት ወይም ሥልጣን ለማግኘት ልትጠቀምበት ትችል ይሆናል። ወይም ደግሞ ልክ እንደ ሙሴ በሕይወትህ ውስጥ ትርጉም ያለው ነገር ለማከናወን ልትመርጥ ትችላለህ። እውቀትህንና ችሎታህን ተጠቅመህ አምላክን ማገልገል እና ሌሎችን መርዳት ትችላለህ። (ማቴዎስ 22:35-40) ደግሞም ከዚህ ይበልጥ እርካታ የሚያስገኝ ነገር የለም!