በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

አርዓያ የሚሆኑ ሰዎች—ሩት

አርዓያ የሚሆኑ ሰዎች—ሩት

አርዓያ የሚሆኑ ሰዎች—ሩት

ሩት በታማኝነት ረገድ ግሩም ምሳሌ ትሆናለች። በትውልድ አገሯ የተመቻቸ ሕይወት መምራት ትችል የነበረ ቢሆንም በዕድሜ ከገፋችው አማቷ ከኑኃሚን ጋር ለመኖር መርጣለች። ባሏን በሞት ያጣችው ይህች ሴት ከአማቷ ጋር ለመኖር መምረጧ ሌላ የትዳር ጓደኛ የማግኘት አጋጣሚዋን የሚያጠብበው ቢሆንም ከራሷ ፍላጎት ይበልጥ ትኩረት የሰጠችው ሌላ ነገር ነበር። ለኑኃሚን ፍቅር ያላት ከመሆኑም በላይ በይሖዋ ሕዝቦች መካከል ለመኖር ትፈልግ ነበር፤ ለማግባት ካላት ፍላጎት የበለጠ ትልቅ ቦታ የሰጠችው ለእነዚህ ነገሮች ነው።—ሩት 1:8-17

ለማግባት እያሰብህ ነው? ከሆነ የሩትን ምሳሌ ተከተል። ስለ ራስህ ስሜት ብቻ ከማሰብ ይልቅ በትዳር ውስጥ ልታንጸባርቃቸው የምትችላቸው ምን አስፈላጊ ባሕርያት እንዳሉህ ለማወቅ ራስህን ገምግም። ለምሳሌ ያህል ታማኝ እና የራስህን ጥቅም መሥዋዕት የምታደርግ ሰው ነህ? ፍጹም አለመሆንህ ትክክል ያልሆነውን እንድታደርግ ተጽዕኖ ቢያሳድርብህም እንኳ የአምላክን መመሪያዎች ታከብራለህ? ሩት ትዳር መመሥረትን ከምንም በላይ አስበልጣ አልተመለከተችውም። ያም ቢሆን ከጊዜ በኋላ እንደ እሷ ዓይነት ባሕርያት ያሉት፣ ብስለት ያለውና ከሁሉ በላይ ደግሞ አምላክን የሚወድ ባል አግኝታለች። አንተም እንደዚህ ዓይነት ትዳር ማግኘት ትችላለህ።