በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች!

ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች!

መቅድም

ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች!

‘ከወላጆቼ ጋር መነጋገር የምችለው እንዴት ነው?’ ‘ጓደኞች ማፍራት የምችለው እንዴት ነው?’ ‘የፍቅር ጓደኝነት ሳይኖር ካገኙት ሰው ጋር የፆታ ግንኙነት መፈጸም ምን ስህተት አለው?’ ‘ይህን ያህል የማዝነው ለምንድን ነው?’

ከላይ ያሉት ጥያቄዎች የሚያሳስቡህ ከሆነ እንዲህ የሚሰማህ አንተ ብቻ አይደለህም። ለጥያቄዎችህ መልስ ስትፈልግ ደግሞ እርስ በርስ የሚጋጩ ሐሳቦች አግኝተህ ይሆናል። ንቁ! መጽሔት፣ ወጣቶች እምነት ሊጣልበት የሚችል ምክር እንዲያገኙ ለመርዳት ሲል ከጥር 1982 አንስቶ “የወጣቶች ጥያቄ . . .” የተባለ ዓምድ በተከታታይ ይዞ መውጣት ጀመረ። በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ሐሳቦችን የያዘው ይህ ዓምድ አሁንም በአንባቢዎች ዘንድ ተወዳጅ ነው። በዚህ ዓምድ ላይ የሚወጣው እያንዳንዱ ርዕስ የተጻፈው ጥልቀት ያለው ምርምር ከተደረገ በኋላ ነው። እንዲያውም የንቁ! ጸሐፊዎች የወጣቶችን አመለካከትና ስሜት ለማወቅ ሲሉ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችን አነጋግረዋል! ከሁሉ በላይ ደግሞ “የወጣቶች ጥያቄ” በተባለው ዓምድ ላይ የሰፈረው ምክር በአምላክ ቃል ይኸውም በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ ነው።

ይህ መጽሐፍ ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀው በ1989 ነው። ይሁን እንጂ በዛሬው ጊዜ ያሉ ወጣቶች የሚያጋጥሟቸውን ሁኔታዎች ለማካተት ሲባል በዚህ መጽሐፍ ላይ ምዕራፎቹ በአዲስ መልክ ተዘጋጅተዋል። በመጽሐፉ ላይ የሚገኙት ከ30 የሚበልጡ ምዕራፎች የተወሰዱት ከ2004 እስከ 2011 ባሉት ዓመታት በንቁ! መጽሔት ላይ “የወጣቶች ጥያቄ” በሚለው ዓምድ ሥር ከወጡት ርዕሶች ነው።

ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች፣ ጥራዝ 1 የተባለው መጽሐፍ፣ ኃላፊነት የሚሰማህ አዋቂ ሰው ለመሆን የሚረዱህን ጠቃሚ ሐሳቦች የያዘ ነው። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወጣቶችና አዋቂዎች “ትክክልና ስህተት የሆነውን ነገር መለየት እንዲችሉ የማስተዋል ችሎታቸውን በማሠራት [ማሠልጠን]” ችለዋል፤ አንተም በዚህ መጽሐፍ ላይ የሚገኙትን ምክሮች በተግባር በማዋል እንደ እነሱ ማድረግ እንደምትችል ተስፋ እናደርጋለን።—ዕብራውያን 5:14

አዘጋጆቹ