በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የአምላክ ፈቃድ ምንድን ነው?

የአምላክ ፈቃድ ምንድን ነው?

አምላክ ገነት በምትሆነው ምድር ላይ በሰላምና በደስታ ለዘላለም እንድንኖር ይፈልጋል!

‘ይህማ እንዴት ሊሆን ይችላል?’ ብለህ ታስብ ይሆናል። የአምላክ መንግሥት እንዲህ ዓይነት ዓለም እንደሚያመጣ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል፤ የአምላክ ፈቃድ ሁሉም ሰው ስለዚህ መንግሥትና አምላክ ለእኛ ስላለው ዓላማ እንዲያውቅ ነው።—መዝሙር 37:11, 29፤ ኢሳይያስ 9:7

አምላክ ራሳችንን እንድንጠቅም ይፈልጋል።

አንድ ጥሩ አባት፣ ልጆቹ ከሁሉ የተሻለውን ነገር እንዲያገኙ እንደሚመኝ ሁሉ የሰማዩ አባታችንም ዘላለማዊ ደስታ እንድናገኝ ይፈልጋል። (ኢሳይያስ 48:17, 18) “የአምላክን ፈቃድ የሚያደርግ” ሁሉ ‘ለዘላለም እንደሚኖር’ ቃል ገብቷል።—1 ዮሐንስ 2:17

አምላክ በጎዳናው እንድንሄድ ይፈልጋል።

ፈጣሪያችን ‘በጎዳናዎቹ መሄድ እንድንችል’ ለመርዳት ‘መንገዶቹን እንደሚያስተምረን’ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። (ኢሳይያስ 2:2, 3) እንዲሁም ፈቃዱ በመላው ምድር እንዲታወቅ ሲል “ከአሕዛብ መካከል ለስሙ የሚሆኑ ሰዎችን” በመውሰድ አደራጅቷቸዋል።—የሐዋርያት ሥራ 15:14

አምላክ የእሱ አምላኪዎች አንድነት እንዲኖራቸው ይፈልጋል።

የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ፣ ሰዎችን ከመከፋፈል ይልቅ እውነተኛ በሆነ ፍቅር አንድ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል። (ዮሐንስ 13:35) በዛሬው ጊዜ በየትኛውም ቦታ የሚኖሩ ሰዎች አምላክን በአንድነት ማገልገል የሚችሉት እንዴት እንደሆነ የሚያስተምሩት እነማን ናቸው? የዚህን ጥያቄ መልስ ከዚህ ብሮሹር ላይ እንድታነብ እንጋብዝሃለን።