በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ትምህርት 4

አዲስ ዓለም ትርጉም የተባለውን መጽሐፍ ቅዱስ ያዘጋጀነው ለምንድን ነው?

አዲስ ዓለም ትርጉም የተባለውን መጽሐፍ ቅዱስ ያዘጋጀነው ለምንድን ነው?

ኮንጎ (ኪንሻሳ)

ሩዋንዳ

መለኮታዊው ስም በመዝሙር 69:31 ላይ የሚገኝበት የሲማከስ ቅጂ ቁራጭ፣ በሦስተኛው ወይም በአራተኛው መቶ ዘመን ዓ.ም. የተዘጋጀ

የይሖዋ ምሥክሮች ለበርካታ አሥርተ ዓመታት የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞችን ተጠቅመዋል፤ አትመዋል እንዲሁም አሰራጭተዋል። ይሁንና የአምላክ ፈቃድ ሁሉም ሰው “የእውነትን ትክክለኛ እውቀት” እንዲያገኝ በመሆኑ ይህን ለማድረግ የሚረዳ አዲስ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ማዘጋጀት እንደሚያስፈልግ ከጊዜ በኋላ ተገነዘብን። (1 ጢሞቴዎስ 2:3, 4) በመሆኑም በ1950 በዘመናዊ ቋንቋ ያዘጋጀነውን አዲስ ዓለም ትርጉም የተባለ መጽሐፍ ቅዱስ በከፊል ማውጣት ጀመርን። በአሁኑ ጊዜ ከ130 በሚበልጡ ቋንቋዎች በተተረጎመው በዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የመጀመሪያውን የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት በታማኝነትና በትክክል ለማስተላለፍ ጥረት ተደርጓል።

ለመረዳት የማይከብድ መጽሐፍ ቅዱስ ያስፈልግ ነበር። ቋንቋዎች በጊዜ ሂደት እየተለወጡ ይሄዳሉ፤ በመሆኑም በብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ውስጥ የሚገኙት ቃላትና አገላለጾች የቆዩና ለመረዳት የሚያስቸግሩ ከመሆናቸውም ሌላ ግልጽ አይደሉም። በተጨማሪም ይበልጥ ትክክለኛና ለበኩረ ጽሑፉ ቅርብ የሆኑ ብዙ ጥንታዊ የቅዱሳን መጻሕፍት ቅጂዎች በመገኘታቸው መጽሐፍ ቅዱስ ስለተጻፈበት የዕብራይስጥ፣ የአረማይክ እና የግሪክኛ ቋንቋ የተሻለ ግንዛቤ ሊኖር ችሏል።

የአምላክን ቃል ምንም ሳይለውጥ በታማኝነት የሚያስተላልፍ ትርጉም ያስፈልግ ነበር። የመጽሐፍ ቅዱስ ተርጓሚዎች በመንፈስ መሪነት የተጻፈውን የአምላክ ቃል እንዳሻቸው ከመለወጥ ይልቅ የበኩረ ጽሑፉን ሐሳብ ምንም ሳይለውጡ ማስተላለፍ ይኖርባቸዋል። አብዛኞቹ ትርጉሞች ግን ይሖዋ የሚለውን መለኮታዊ ስም ከቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ አውጥተውታል።

ለመጽሐፍ ቅዱስ ባለቤት እውቅና የሚሰጥ ትርጉም ያስፈልግ ነበር። (2 ሳሙኤል 23:2) ከታች ባለው ሥዕል ላይ እንደሚታየው በጥንቶቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎች ውስጥ 7,000 ጊዜ ያህል ይገኝ የነበረው የይሖዋ ስም በአዲስ ዓለም ትርጉም ውስጥ ትክክለኛው ቦታው ላይ ተመልሷል። (መዝሙር 83:18) ለበርካታ ዓመታት ጥልቅ ምርምር ከተደረገ በኋላ የተዘጋጀው ይህ መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክን ሐሳብ በትክክል የሚያስተላልፍ በመሆኑ ለማንበብ ያስደስታል። አዲስ ዓለም ትርጉም በራስህ ቋንቋ ኖረም አልኖረ የይሖዋን ቃል በየቀኑ የማንበብ ልማድ እንድታዳብር እናበረታታሃለን።—ኢያሱ 1:8፤ መዝሙር 1:2, 3

  • አዲስ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ያዘጋጀነው ለምንድን ነው?

  • የአምላክን ፈቃድ ማወቅ የሚፈልግ ማንኛውም ሰው በየቀኑ ምን የማድረግ ልማድ ቢኖረው ጥሩ ነው?