በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በስተ ግራ፦ በ1946 በስዊዘርላንድ ያሉ ወንድሞች በጀርመን ላሉ ወንድሞቻችን የእርዳታ ቁሳቁስ ልከዋል፤ በስተ ቀኝ፦ በ2011 ጃፓን በሱናሚ ከተመታች በኋላ የመንግሥት አዳራሽ እንደገና ሲሠራ

ክፍል 6

መንግሥቱን መደገፍ—የአምልኮ ቦታዎችን መገንባትና እርዳታ ማቅረብ

መንግሥቱን መደገፍ—የአምልኮ ቦታዎችን መገንባትና እርዳታ ማቅረብ

ወደ መንግሥት አዳራሻችሁ ስትገባ ሁሉ ነገር ተለዋውጧል። የመንግሥት አዳራሹን ስታየው ሁልጊዜ ኩራት ይሰማሃል። ከተወሰኑ ዓመታት በፊት አዳራሹ ሲገነባ በሥራው ስለተካፈልህ አስደሳች ትዝታዎች አሉህ። አሁን ደግሞ የመንግሥት አዳራሹ ጊዜያዊ የእርዳታ ማዕከል ሆኖ ማገልገል መቻሉን ስታይ ይበልጥ ኩራት ይሰማሃል። በአካባቢያችሁ የተከሰተው የጎርፍ መጥለቅለቅ ከፍተኛ ውድመት በማስከተሉ ቅርንጫፍ ኮሚቴው በአደጋው የተጎዱት ሰዎች ምግብ፣ ልብስ፣ ንጹሕ ውኃና ሌሎች አስፈላጊ ነገሮችን እንዲያገኙ ወዲያውኑ ዝግጅት አደረገ። በመንግሥት አዳራሹ ውስጥ የእርዳታ ቁሳቁሶች በሥርዓት ተደርድረዋል። ወንድሞችና እህቶች ወደ አዳራሹ እየመጡ የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች እየወሰዱ ነው፤ የብዙዎቹ ዓይን የደስታ እንባ አቅርሯል።

ኢየሱስ፣ ተከታዮቹን ለይቶ የሚያሳውቃቸው ጉልህ ምልክት አንዳቸው ለሌላው ያላቸው ፍቅር እንደሆነ ተናግሯል። (ዮሐ. 13:34, 35) በዚህ ክፍል ውስጥ፣ የይሖዋ ምሥክሮች የአምልኮ ቦታዎች በመገንባትና አደጋ ለደረሰባቸው እርዳታ በመስጠት ክርስቲያናዊ ፍቅር ያሳዩት እንዴት እንደሆነ እንመረምራለን። እንዲህ ያለው ፍቅር በኢየሱስ መንግሥት አገዛዝ ሥር እንደምንኖር የሚያሳይ ጠንካራ ማስረጃ ነው።

በዚህ ክፍል ውስጥ

ምዕራፍ 18

የመንግሥቱ ሥራዎች ወጪ የሚሸፈንበት መንገድ

ገንዘቡ የሚገኘው እንዴት ነው? ሥራ ላይ የሚውለውስ እንዴት ነው?

ምዕራፍ 19

ይሖዋን የሚያስከብር የግንባታ ሥራ

የአምልኮ ቦታዎች ለይሖዋ ክብር ያመጣሉ፤ ይሁንና ይሖዋ ይበልጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ለእነዚህ ነገሮች አይደለም።

ምዕራፍ 20

የእርዳታ አገልግሎት

የእርዳታ ሥራ ለይሖዋ የምናቀርበው ቅዱስ አገልግሎት ክፍል መሆኑን እንዴት እናውቃለን?