በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ትምህርት 6

ስምንት ሰዎች ከጥፋት ውኃው ተረፉ

ስምንት ሰዎች ከጥፋት ውኃው ተረፉ

ኖኅ፣ ቤተሰቡ እና እንስሳቱ ወደ መርከቡ ገቡ። ይሖዋም በሩን ዘጋው፤ ከዚያም ዝናብ መዝነብ ጀመረ። ዝናቡ በጣም ኃይለኛ ከመሆኑ የተነሳ መርከቡ መንሳፈፍ ጀመረ። በኋላም መላዋ ምድር በውኃ ተሸፈነች። ከመርከቡ ውጭ ያሉት ክፉ ሰዎች በሙሉ ሞቱ። ኖኅና ቤተሰቡ ግን መርከቡ ውስጥ በመሆናቸው ምንም አደጋ አልደረሰባቸውም። ይሖዋን በመታዘዛቸው ምን ያህል ተደስተው እንደሚሆን መገመት ትችላለህ?

ዝናቡ 40 ቀንና 40 ሌሊት ከዘነበ በኋላ መዝነቡን አቆመ። የውኃው መጠን ቀስ በቀስ እየቀነሰ መጣ። በመጨረሻም መርከቡ ተራራ ላይ አረፈ። ሆኖም ውኃው ገና በደንብ ስላልቀነሰ ኖኅና ቤተሰቡ ከመርከቡ መውጣት አልቻሉም።

ቀስ በቀስ ውኃው እየደረቀ መጣ። ኖኅና ቤተሰቡ ከአንድ ዓመት በላይ መርከቡ ውስጥ ቆይተዋል። ከዚያም ይሖዋ፣ ከመርከቡ ወጥተው አዲስ ወደሆነው ዓለም መግባት እንደሚችሉ ነገራቸው። ኖኅና ቤተሰቡ ይሖዋ ስላዳናቸው በጣም ተደሰቱ፤ ምስጋናቸውንም ለመግለጽ ለይሖዋ መባ አቀረቡ።

ይሖዋ ባቀረቡት መባ ተደሰተ። ምድር ላይ ያለውን ነገር ሁሉ በድጋሚ በውኃ እንደማያጠፋ ቃል ገባ። ለገባው ቃል ምልክት እንዲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ቀስተ ደመና በሰማይ ላይ እንዲታይ አደረገ። ቀስተ ደመና አይተህ ታውቃለህ?

ከዚያም ይሖዋ ኖኅንና ቤተሰቡን ልጆች ወልደው ምድርን እንዲሞሉ ነገራቸው።

“የጥፋት ውኃ መጥቶ ሁሉንም ጠራርጎ እስከወሰዳቸው ጊዜ ድረስ [ሰዎቹ] ምንም አላስተዋሉም።”—ማቴዎስ 24:38, 39