በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ትምህርት 74

ኢየሱስ መሲሕ ሆነ

ኢየሱስ መሲሕ ሆነ

መጥምቁ ዮሐንስ ‘ከእኔ የሚበልጥ ይመጣል’ እያለ ይሰብክ ነበር። ኢየሱስ 30 ዓመት ሲሆነው ከገሊላ ተነስቶ ዮሐንስ ወደሚያጠምቅበት ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ መጣ። ኢየሱስ፣ ዮሐንስ እንዲያጠምቀው ፈልጎ ነበር፤ ዮሐንስ ግን ‘እኔ አንተን ማጥመቅ የለብኝም። እንዲያውም እኔን ማጥመቅ ያለብህ አንተ ነህ’ አለው። ኢየሱስ ግን ዮሐንስን ‘ይሖዋ፣ አንተ እንድታጠምቀኝ ይፈልጋል’ አለው። ስለዚህ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ገቡ፤ ዮሐንስም ኢየሱስን ሙሉ በሙሉ ውኃው ውስጥ በማጥለቅ አጠመቀው።

ኢየሱስ ከውኃው ከወጣ በኋላ ጸለየ። ወዲያውኑም ሰማያት ተከፈቱ፤ የአምላክም መንፈስ በእሱ ላይ እንደ ርግብ ወረደ። ከዚያም ይሖዋ ከሰማይ እንዲህ በማለት ተናገረ፦ “አንተ የምወድህ ልጄ ነህ፤ በአንተ ደስ ይለኛል።”

ኢየሱስ የይሖዋ መንፈስ ሲወርድበት መሲሕ ወይም ክርስቶስ ሆነ። ከዚያም ይሖዋ በምድር ላይ እንዲያከናውነው የሰጠውን ሥራ መሥራት ጀመረ።

ኢየሱስ ከተጠመቀ በኋላ ወደ ምድረ በዳ ሄዶ በዚያ 40 ቀን ቆየ። ከምድረ በዳ ሲመለስ ወደ ዮሐንስ ሄደ። ዮሐንስ፣ ኢየሱስ ወደ እሱ ሲመጣ አይቶ ‘የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግደው የአምላክ በግ ይህ ነው’ አለ። ዮሐንስ ይህን ሲል ኢየሱስ መሲሕ መሆኑን ለሕዝቡ ማሳወቁ ነበር። ኢየሱስ በምድረ በዳ በነበረበት ወቅት ምን እንዳጋጠመው ታውቃለህ? እስቲ እንመልከት።

“‘አንተ የምወድህ ልጄ ነህ፤ በአንተ ደስ ይለኛል’ የሚል ድምፅ ከሰማያት መጣ።”—ማርቆስ 1:11