በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የክፍል 1 ማስተዋወቂያ

የክፍል 1 ማስተዋወቂያ

መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ስንጀምር ስለ አምላክ የፍጥረት ሥራ የሚገልጽ ታሪክ እናገኛለን፤ ይህ ታሪክ ይሖዋ በሰማይም ሆነ በምድር ስለፈጠራቸው ውብ ነገሮች እንድናውቅ ያስችለናል። ወላጅ ከሆንክ ልጅህ፣ ይሖዋ የፈጠራቸውን ብዙ ዓይነት ፍጥረታት እንዲያስተውል እርዳው። አምላክ የሰው ልጆችን ከእንስሳት እጅግ የላቁ አድርጎ እንደፈጠራቸው ይኸውም የመናገር፣ የማገናዘብ፣ አዳዲስ ነገሮችን የመፈልሰፍ፣ የመዘመርና የመጸለይ ችሎታ እንደሰጣቸው ግለጽለት። የይሖዋን ኃይልና ጥበብ በተለይ ደግሞ እኛን ጨምሮ ለፍጥረታቱ በሙሉ ያሳየውን ፍቅር እንዲያደንቅ እርዳው።

በዚህ ክፍል ውስጥ

ትምህርት 1

አምላክ ሰማይንና ምድርን ሠራ

መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ ሰማይንና ምድርን እንደፈጠረ ይናገራል። አምላክ ሌሎች ነገሮችን ሁሉ ከመፍጠሩ በፊት አንድ መልአክ የፈጠረው ለምንድን ነው?

ትምህርት 2

አምላክ የመጀመሪያዎቹን ወንድና ሴት ፈጠረ

አምላክ የመጀመሪያዎቹን ወንድና ሴት ከፈጠረ በኋላ በኤደን የአትክልት ስፍራ አስቀመጣቸው። ቤተሰብ መሥርተው መላዋን ምድር ገነት እንዲያደርጉ ፈልጎ ነበር።