በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የክፍል 7 ማስተዋወቂያ

የክፍል 7 ማስተዋወቂያ

ይህ ክፍል የንጉሥ ሳኦልንና የንጉሥ ዳዊትን የሕይወት ታሪክ የያዘ ሲሆን ወደ 80 በሚጠጉ ዓመታት ውስጥ የተከናወኑ ነገሮችን ያወሳል። ሳኦል መጀመሪያ ላይ ትሑትና አምላክን የሚፈራ ሰው ነበር፤ ከጊዜ በኋላ ግን የአምላክን መመሪያ ለመቀበል ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል። በዚህም የተነሳ ይሖዋ ሳኦልን ተወው፤ ከዚያም ዳዊትን የእስራኤል ንጉሥ አድርጎ እንዲቀባው ሳሙኤልን አዘዘው። ሳኦል በቅናት ተነሳስቶ ዳዊትን ለመግደል በተደጋጋሚ ቢሞክርም ዳዊት ለመበቀል አልሞከረም። የሳኦል ልጅ ዮናታን፣ ይሖዋ የመረጠው ዳዊትን እንደሆነ ስለተገነዘበ ለዳዊት ታማኝ ሆኗል። ዳዊት ከባድ ኃጢአት የሠራባቸው ጊዜያት ቢኖሩም ምንጊዜም የይሖዋን ተግሣጽ ለመቀበል ፈቃደኛ ነበር። ወላጅ ከሆንክ፣ ልጅህ የይሖዋን ዝግጅቶች መደገፍ ያለውን ጥቅም እንዲገነዘብ እርዳው።

በዚህ ክፍል ውስጥ

ትምህርት 39

የመጀመሪያው የእስራኤል ንጉሥ

አምላክ ለእስራኤላውያን የሚመሯቸው መሳፍንት ሰጥቷቸው የነበረ ቢሆንም እስራኤላውያን ንጉሥ እንዲሾምላቸው ፈለጉ። ሳሙኤል ሳኦልን የመጀመሪያው ንጉሥ እንዲሆን ቀባው፤ በኋላ ግን ይሖዋ ሳኦልን ትቶ ሌላ ንጉሥ ለመሾም ወሰነ። ለምን?

ትምህርት 40

ዳዊት እና ጎልያድ

ይሖዋ ቀጣዩ የእስራኤል ንጉሥ እንዲሆን ዳዊትን መረጠው፤ ዳዊት ያደረገው ነገር እሱ ንጉሥ እንዲሆን መመረጡ ተገቢ እንደሆነ የሚያሳይ ነው።

ትምህርት 41

ዳዊት እና ሳኦል

ሳኦል ዳዊትን የጠላው ለምንድን ነው? ዳዊትስ ምን ምላሽ ሰጠ?

ትምህርት  42

ዮናታን ደፋርና ታማኝ ነበር

የንጉሡ ልጅ የዳዊት ጓደኛ ሆነ።

ትምህርት 43

ንጉሥ ዳዊት የሠራው ኃጢአት

ዳዊት ያደረገው መጥፎ ውሳኔ ብዙ ችግር አስከትሏል።