በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የክፍል 9 ማስተዋወቂያ

የክፍል 9 ማስተዋወቂያ

በዚህ ክፍል ውስጥ በይሖዋ ላይ አስደናቂ እምነት ስላሳዩ ወጣቶች፣ ነቢያትና ነገሥታት እንማራለን። ሶርያ ውስጥ የምትኖር አንዲት ትንሽ እስራኤላዊት ልጅ የይሖዋ ነቢይ ንዕማንን እንደሚያድነው እምነት ነበራት። ነቢዩ ኤልሳዕ፣ ይሖዋ ከጠላት ሠራዊት እንደሚያድነው ሙሉ እምነት ነበረው። ሊቀ ካህናቱ ዮዳሄ ሕፃኑን ኢዮዓስን ክፉ ከሆነችው ከአያቱ ከጎቶልያ እጅ ለማዳን ሕይወቱን አደጋ ላይ ጥሏል። ንጉሥ ሕዝቅያስ ይሖዋ ኢየሩሳሌምን ከጠላት እንደሚታደጋት ስለተማመነ አሦራውያንን ፈርቶ እጅ አልሰጠም። ንጉሥ ኢዮስያስ ጣዖት አምልኮን አስወገደ፤ ቤተ መቅደሱን አደሰ፤ እንዲሁም ሕዝቡ ወደ እውነተኛው አምልኮ እንዲመለስ አደረገ።

በዚህ ክፍል ውስጥ

ትምህርት 51

የሠራዊቱ አለቃና ትንሿ ልጅ

አንዲት ትንሽ እስራኤላዊት ልጅ ይሖዋ ስላለው ታላቅ ኃይል ለእመቤቷ ነገረቻት፤ ይህም አስገራሚ ውጤት አስገኘ።

ትምህርት 52

የይሖዋ የእሳት ፈረሶችና የጦር ሠረገሎች

የኤልሳዕ አገልጋይ፣ ኤልሳዕ ‘ከእነሱ ጋር ካሉት ከእኛ ጋር ያሉት ይበልጣሉ’ ያለው ለምን እንደሆነ ማስተዋል ቻለ።

ትምህርት 53

ዮዳሄ ያሳየው ድፍረት

አንድ ታማኝ ካህን አንዲትን ክፉ ንግሥት ተቃወማት።

ትምህርት 54

ይሖዋ ዮናስን በትዕግሥት አስተማረው

አንድ የአምላክ ነቢይ በትልቅ ዓሣ የተዋጠው ለምንድን ነው? ከዓሣው ሆድ የወጣውስ እንዴት ነው? ይሖዋ ዮናስን ምን አስተማረው?

ትምህርት 55

የይሖዋ መልአክ ሕዝቅያስን አዳነው

የይሁዳ ጠላቶች ይሖዋ ሕዝቡን አይጠብቅም ብለው ነበር፤ ሆኖም ተሳስተዋል!

ትምህርት 56

ኢዮስያስ የአምላክን ሕግ ይወድ ነበር

ኢዮስያስ የስምንት ዓመት ልጅ ሳለ ንጉሥ ሆነ፤ ሕዝቡንም ይሖዋን እንዲያመልኩ ረዳቸው።