በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የክፍል 12 ማስተዋወቂያ

የክፍል 12 ማስተዋወቂያ

ኢየሱስ ለሰዎች ስለ መንግሥተ ሰማያት አስተምሯል። እንዲሁም የአምላክ ስም እንዲቀደስ፣ መንግሥቱ እንዲመጣና ፈቃዱ በምድር ላይ እንዲፈጸም እንዲጸልዩ አስተምሯቸዋል። ወላጅ ከሆንክ ልጅህ ይህ ጸሎት ለእኛ ምን ትርጉም እንዳለው እንዲገነዘብ እርዳው። ኢየሱስ በሰይጣን ፈተና ተሸንፎ ታማኝነቱን አላጓደለም። ከጊዜ በኋላ ሐዋርያቱን መረጠ፤ እነሱም የአምላክ መንግሥት የመጀመሪያ አባላት ከመሆናቸውም ሌላ በመንግሥቱ ውስጥ ትልቅ ሚና ይጫወታሉ። ኢየሱስ ለእውነተኛው አምልኮ ከፍተኛ ቅንዓት አሳይቷል። ሰዎችን የመርዳት ፍላጎት ስለነበረው የታመሙትን ፈውሷል፤ የተራቡትን መግቧል፤ እንዲሁም የሞቱትን አስነስቷል። እነዚህን ተአምራት በመፈጸም የአምላክ መንግሥት ለሰው ልጆች ምን በረከት እንደሚያመጣ አሳይቷል።

በዚህ ክፍል ውስጥ

ትምህርት 74

ኢየሱስ መሲሕ ሆነ

ዮሐንስ ኢየሱስን ‘የአምላክ በግ’ በማለት ሲጠራው ምን ማለቱ ነበር?

ትምህርት 75

ዲያብሎስ ኢየሱስን ፈተነው

ዲያብሎስ ኢየሱስን ሦስት ጊዜ ፈተነው። ሦስቱ ፈተናዎች የትኞቹ ናቸው? ኢየሱስስ ምን ምላሽ ሰጠ?

ትምህርት 76

ኢየሱስ ነጋዴዎችን ከቤተ መቅደሱ አባረረ

ኢየሱስ እንስሳቱን ከቤተ መቅደሱ ያባረረውና የገንዘብ መንዛሪዎችን ጠረጴዛ የገለባበጠው ለምንድን ነው?

ትምህርት 77

ውኃ ልትቀዳ የመጣችው ሳምራዊት ሴት

አንዲት ሳምራዊት ሴት ኢየሱስ ሲያነጋግራት በጣም ተገረመች። ለምን? ኢየሱስ ለሌላ ለማንም ሰው ያልተናገረውን ምን ነገር ነገራት?

ትምህርት 78

ኢየሱስ የአምላክን መንግሥት ምሥራች ሰበከ

ኢየሱስ አንዳንድ ደቀ መዛሙርቱን “ሰው አጥማጆች” እንዲሆኑ ጥሪ አቀረበላቸው። ከጊዜ በኋላም ከተከታዮቹ መካከል 70ዎቹን ምሥራቹን እንዲሰብኩ አሠለጠናቸው።

ትምህርት 79

ኢየሱስ ብዙ ተአምራት ፈጽሟል

ኢየሱስ በሄደበት ቦታ ሁሉ፣ የታመሙ ሰዎች ከበሽታቸው እንዲያድናቸው ወደ እሱ ይመጡ ነበር፤ እሱም ሁሉንም ፈውሷቸዋል። አንዲትን የሞተች ልጅ እንኳ አስነስቷል።

ትምህርት 80

ኢየሱስ አሥራ ሁለት ሐዋርያትን መረጠ

ኢየሱስ የመረጣቸው ለምንድን ነው? ስማቸውን ታስታውሳለህ?

ትምህርት 81

የተራራው ስብከት

ኢየሱስ ለተሰበሰበው ሕዝብ ጠቃሚ ትምህርት ሰጠ።

ትምህርት 82

ኢየሱስ ስለ ጸሎት አስተማረ

ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ስለ የትኞቹ ነገሮች ደጋግመው እንዲለምኑ ነግሯቸዋል?

ትምህርት 83

ኢየሱስ ብዙ ሰዎችን መገበ

ይህ ተአምር ኢየሱስንና ይሖዋን በተመለከተ ምን ያስተምረናል?

ትምህርት 84

ኢየሱስ በውኃ ላይ ሄደ

ሐዋርያቱ ይህ ተአምር ሲፈጸም ሲያዩ ምን ተሰምቷቸው ሊሆን እንደሚችል መገመት ትችላለህ?

ትምህርት 85

ኢየሱስ በሰንበት ቀን አንድን ዓይነ ስውር ፈወሰ

ኢየሱስ ባደረገው ነገር አንዳንድ ሰዎች ያልተደሰቱት ለምንድን ነው?

ትምህርት 86

ኢየሱስ አልዓዛርን ከሞት አስነሳው

ኢየሱስ ማርያም ስታለቅስ ሲያይ እሱም ማልቀስ ጀመረ። ሆኖም ሐዘናቸው ወዲያውኑ በደስታ ተተካ።