በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የክፍል 14 ማስተዋወቂያ

የክፍል 14 ማስተዋወቂያ

የጥንቶቹ ክርስቲያኖች የመንግሥቱን ምሥራች እስከ ምድር ዳር ድረስ ሰበኩ። ኢየሱስ ለእነዚህ ክርስቲያኖች የት መስበክ እንዳለባቸው መመሪያ ሰጥቷቸው ነበር፤ እንዲሁም ሰዎችን በየራሳቸው ቋንቋ ማስተማር እንዲችሉ ተአምራዊ በሆነ መንገድ ረድቷቸዋል። ይሖዋ ድፍረትና የሚደርስባቸውን ከባድ ስደት ለመቋቋም የሚያስችል ኃይል ሰጥቷቸዋል።

ኢየሱስ ለሐዋርያው ዮሐንስ የይሖዋን ክብር በራእይ አሳየው። ከዚህም ሌላ ዮሐንስ የአምላክ መንግሥት ሰይጣንን ድል ሲነሳና የሰይጣንን ግዛት ለዘላለም ሲደመስስ በራእይ ተመልክቷል። ዮሐንስ ንጉሡን ኢየሱስንና 144,000 ተባባሪ ገዢዎቹን አይቷል። በተጨማሪም መላዋ ምድር ይሖዋን በሰላምና በአንድነት የሚያመልኩ ሰዎች የሚኖሩባት ገነት ስትሆን በራእይ ተመልክቷል።

በዚህ ክፍል ውስጥ

ትምህርት 94

የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት መንፈስ ቅዱስ ተቀበሉ

መንፈስ ቅዱስ ለኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ምን ተአምራዊ ችሎታ ሰጣቸው?

ትምህርት 95

ምንም ነገር ሊያስቆማቸው አልቻለም

ኢየሱስን ያስገደሉት የሃይማኖት መሪዎች ደቀ መዛሙርቱን ዝም ለማሰኘት ሞከሩ። ሆኖም አልተሳካላቸውም።

ትምህርት 96

ኢየሱስ ሳኦልን መረጠው

ሳኦል የክርስቲያኖች ቀንደኛ ጠላት ነበር፤ ሆኖም ሕይወቱን የሚለውጥ ነገር አጋጠመው።

ትምህርት 97

ቆርኔሌዎስ መንፈስ ቅዱስ ተቀበለ

አምላክ ጴጥሮስን አይሁዳዊ ወዳልሆነው ወደዚህ ሰው ቤት የላከው ለምንድን ነው?

ትምህርት 98

ክርስትና ወደ ብዙ አገሮች ተስፋፋ

ሐዋርያው ጳውሎስና የአገልግሎት ጓደኞቹ ርቀው በሚገኙ ቦታዎች መስበክ ጀመሩ።

ትምህርት 99

አንድ የእስር ቤት ጠባቂ ክርስቲያን ሆነ

ጳውሎስና ሲላስ የታሰሩት ለምንድን ነው? የእስር ቤቱ ጠባቂ እውነትን የተማረው እንዴት ነው?

ትምህርት 100

ጳውሎስና ጢሞቴዎስ

ሁለቱ ሰዎች ለብዙ ዓመታት ጓደኛሞች ሆነው ኖረዋል፤ እንዲሁም ይሖዋን አብረው አገልግለዋል።

ትምህርት 101

ጳውሎስ ወደ ሮም ተወሰደ

ጉዞው በጣም አደገኛ ነበር፤ ሆኖም የትኛውም ችግር ቢሆን ይህን ሐዋርያ ሊያስቆመው አልቻለም።

ትምህርት 102

የዮሐንስ ራእይ

ኢየሱስ ስለ ወደፊቱ ጊዜ የሚገልጹ ራእዮችን አሳየው።

ትምህርት 103

“መንግሥትህ ይምጣ”

የዮሐንስ ራእይ የአምላክ መንግሥት ምድርን በሚገዛበት ወቅት የሰው ልጆች ምን ዓይነት ሕይወት እንደሚኖራቸው ይገልጻል።