በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 10

ይሖዋ አምላካችንን አወድሱ!

ይሖዋ አምላካችንን አወድሱ!

(መዝሙር 145:12)

  1. 1. ይወደስ! ይሖዋ አምላክ!

    ክብራማው ስሙም ይታወቅ!

    ተናገር ቀኑ መቅረቡን፤

    ሰዎች ሁሉ ይስሙ ጥሪውን።

    ልጁ ’ሚገዛበት ጊዜ ደርሷል፤

    ይሖዋ ራሱ ተናግሯል።

    ’ሚያመጣውን በረከት በሙሉ፣

    ተናገር ለሰዎች ሁሉ!

    (አዝማች)

    ይወደስ! ይሖዋ አምላክ!

    ታላቅነቱን ዓለም ይወቅ!

  2. 2. ይወደስ! እልል በሉለት!

    ስሙንም ከፍ አድርጉለት!

    ምስጋና ሞልቶት ልባችን፣

    ያወድሰው አንደበታችን።

    ኃያል ቢሆንም ትሑት አምላክ ነው፤

    ጥሩነቱ ወደር የለው።

    ደግ ነው፤ ’ሚያስፈልገንን ያውቃል፤

    ልመናችንን ይሰማል።

    (አዝማች)

    ይወደስ! ይሖዋ አምላክ!

    ታላቅነቱን ዓለም ይወቅ!

(በተጨማሪም መዝ. 89:27⁠፤ 105:1⁠ን እና ኤር. 33:11⁠ን ተመልከት።)