በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 15

የይሖዋን በኩር አወድሱ!

የይሖዋን በኩር አወድሱ!

(ዕብራውያን 1:6)

  1. 1. ይክበር ያምላክ በኩር፤

    ይሖዋ ’ምላክ ሾሞታል።

    በረከትን ያፈሳል፤

    እውነት፣ ፍትሕ ያሰፍናል።

    ክብር፣ ግርማ ተላብሷል፤

    ላምላክ ስም ይቀናል።

    ሉዓላዊነቱንም

    ላለም ያሳውቃል።

    (አዝማች)

    ይክበር ያምላክ በኩር!

    ሊወደስ ይገባዋል፤

    ከጽዮን ተራራ ላይ

    አሁን መግዛት ጀምሯል።

  2. 2. ይክበር ያምላክ በኩር፤

    ለኛ ሲል ሞቶልናል።

    ትሑት ነው ቤዛ ከፍሏል፤

    ኃጢያታችን ይሻራል።

    ብቅ አለች በነጭ አምራ፣

    የጌታ ሙሽራ።

    ይህ የሰማይ ጋብቻ፣

    ነው ለጽድቅ ማስረጃ።

    (አዝማች)

    ይክበር ያምላክ በኩር!

    ሊወደስ ይገባዋል፤

    ከጽዮን ተራራ ላይ

    አሁን መግዛት ጀምሯል።

(በተጨማሪም መዝ. 2:6⁠፤ 45:3, 4⁠ን እና ራእይ 19:8⁠ን ተመልከት።)