በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 16

ያህ ልጁን ሾሟል አወድሱት

ያህ ልጁን ሾሟል አወድሱት

(ራእይ 21:2)

  1. 1. በሁሉ ላይ እንዲገዛ

    ይሖዋ ልጁን ሾሟል፤

    ምድር ላይ ፈቃዱ እንዲሆን

    ዙፋኑ በፍትሕ ጸንቷል።

    (አዝማች)

    ያህ ልጁን ሾሟል አወድሱት፤

    እናንተ ታዛዥ ሕዝቦቹ፣

    በታማኝነት ’ምትከተሉት፣

    ኢየሱስን ከፍ አ’ርጉት።

    ያህ ልጁን ሾሟል አወድሱት፤

    አንግሦታል አመስግኑት።

    ያምላክን ቅዱስ ስም እንዲያስከብር

    ቀብቶታል በክብር።

  2. 2. የክርስቶስ ውድ ወንድሞች፣

    እንዳዲስ ተወለዱ።

    ድርሻ አላቸው በመንግሥቱ፤

    ምድርን ገነት ያደርጋሉ።

    (አዝማች)

    ያህ ልጁን ሾሟል አወድሱት፤

    እናንተ ታዛዥ ሕዝቦቹ፣

    በታማኝነት ’ምትከተሉት፣

    ኢየሱስን ከፍ አ’ርጉት።

    ያህ ልጁን ሾሟል አወድሱት፤

    አንግሦታል አመስግኑት።

    ያምላክን ቅዱስ ስም እንዲያስከብር

    ቀብቶታል በክብር።

(በተጨማሪም ምሳሌ 29:4⁠ን፣ ኢሳ. 66:7, 8⁠ን፣ ዮሐ. 10:4⁠ን እና ራእይ 5:9, 10⁠ን ተመልከት።)