መዝሙር 22
በሰማይ የተቋቋመው መንግሥት ይምጣልን!
-
1. ያለህ፣ የነበርክ፣ የምትኖር
ይሖዋ አምላክ ሆይ፣
ለልጅህ ሥልጣን ሰጥተሃል፤
ዙፋኑን ተረክቧል።
የአምላክ መንግሥት ተወልዷል፤
በቅርቡም ምድርን ይገዛል።
(አዝማች)
ማዳን ያምላክ ሆኗል፤
የሱ መንግሥት ተቋቁሟል።
እንጸልይ ሁላችን
ብለን “መንግሥቱ ይምጣልን!”
-
2. ሰይጣን ጊዜው አልቆበታል፤
ጭንቀት፣ ችግር በዝቷል።
ሆኖም አውቀናል እውነቱን፤
ተስፋችን መቅረቡን።
የአምላክ መንግሥት ተወልዷል፤
በቅርቡም ምድርን ይገዛል።
(አዝማች)
ማዳን ያምላክ ሆኗል፤
የሱ መንግሥት ተቋቁሟል።
እንጸልይ ሁላችን
ብለን “መንግሥቱ ይምጣልን!”
-
3. ከሰማይ ተሰማ ደስታ፣
የመላ’ክት እልልታ።
ጠላታቸው ተወርውሯል፤
ከሰማይ ተጥሏል።
የአምላክ መንግሥት ተወልዷል፤
በቅርቡም ምድርን ይገዛል።
(አዝማች)
ማዳን ያምላክ ሆኗል፤
የሱ መንግሥት ተቋቁሟል።
እንጸልይ ሁላችን
ብለን “መንግሥቱ ይምጣልን!”
(በተጨማሪም ዳን. 2:34, 35ን እና 2 ቆሮ. 4:18ን ተመልከት።)