በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 27

የአምላክ ልጆች መገለጥ

የአምላክ ልጆች መገለጥ

(ሮም 8:19)

  1. 1. አምላክ የመረጣቸውን

    በቅርቡ ይገልጣል።

    ከ’የሱስ ጋር ይገዛሉ፤

    ይሆናሉ ኃያል።

    (አዝማች)

    ያምላክ ልጆች ከክርስቶስ

    ጋር ይገለጣሉ።

    በውጊያው ድል ያደርጋሉ፤

    አብረው ይነግሣሉ።

  2. 2. ቀሪዎቹ ቅቡዓንም

    ድምፁን ይሰማሉ፤

    የጌቶች ጌታ ሲመጣ

    ሰማይ ይሄዳሉ።

    (አዝማች)

    ያምላክ ልጆች ከክርስቶስ

    ጋር ይገለጣሉ።

    በውጊያው ድል ያደርጋሉ፤

    አብረው ይነግሣሉ።

    (መሸጋገሪያ)

    ያምላክ ልጆች ከ’የሱስ ጋር

    ሆነው ይዋጋሉ።

    ከበጉ ጋር በጋብቻ

    ይተሳሰራሉ።

    (አዝማች)

    ያምላክ ልጆች ከክርስቶስ

    ጋር ይገለጣሉ።

    በውጊያው ድል ያደርጋሉ፤

    አብረው ይነግሣሉ።

(በተጨማሪም ዳን. 2:34, 35⁠ን፣ 1 ቆሮ. 15:51, 52⁠ን እና 1 ተሰ. 4:15-17⁠ን ተመልከት።)