መዝሙር 35
‘ይበልጥ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ለይታችሁ እወቁ’
-
1. ለመለየት እውነት የሆነውን፣
ለመለየት መልካሙን፣
ለማወቅ ይበልጥ አስፈላጊውን፣
ይገባናል ማስተዋል!
(አዝማች)
አምላካችን ይደሰታል
ክፉን ጠልተን ጥሩን ስንወድ፤
መቅደም ያለበትን
ስናስቀድም
በረከቱን እናገኛለን!
-
2. የመንግሥቱን ምሥራች ከመስበክ፣
ቅኖችን ከመፈለግ፣
ወዳምላክ ከመምራት የተሻለ፣
ሌላ ምን ሥራ አለ?
(አዝማች)
አምላካችን ይደሰታል
ክፉን ጠልተን ጥሩን ስንወድ፤
መቅደም ያለበትን
ስናስቀድም
በረከቱን እናገኛለን!
-
3. አስፈላጊ ነገር ላይ ማተኮር
እርካታ ይሰጠናል፤
ውስጣዊ ሰላም እናገኛለን፤
ልባችን ይረጋጋል።
(አዝማች)
አምላካችን ይደሰታል
ክፉን ጠልተን ጥሩን ስንወድ፤
መቅደም ያለበትን
ስናስቀድም
በረከቱን እናገኛለን!
(በተጨማሪም መዝ. 97:10ን፣ ዮሐ. 21:15-17ን እና ፊልጵ. 4:7ን ተመልከት።)