በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 38

ጠንካራ ያደርግሃል

ጠንካራ ያደርግሃል

(1 ጴጥሮስ 5:10)

  1. 1. አምላክ ምክንያት ኖሮት እውነትን አሰማህ፤

    ከጨለማ ወደ ብርሃን ጠራህ።

    የልብህን ምኞት እሱን መሻትህን፣

    አስተዋለ ጽድቅን መውደድህን።

    ፈቃዱን ለማድረግ ቃል ገብተሃል፤

    እንደ ቀድሞው ዛሬም ይረዳሃል።

    (አዝማች)

    በ’የሱስ ደም ገዝቶሃል፣

    የራሱም አ’ርጎሃል፤

    እናም ያጸናሃል፤

    ያጠነክርሃል።

    እንደ ቀድሞው ይመራሃል፤

    ይጠብቅሃል።

    አዎ ያጸናሃል፤

    ያጠነክርሃል።

  2. 2. ውድ ልጁን አምላክ ላንተ ሲል ሰጥቶሃል፤

    እንዲሳካልህም ይፈልጋል።

    ውድ ልጁን ላንተ መስጠት ካላሳሳው፣

    ያጸናሃል አትጠራጠረው።

    እምነትና ፍቅርህን አይረሳም፤

    መንከባከቡን አያቋርጥም።

    (አዝማች)

    በ’የሱስ ደም ገዝቶሃል፣

    የራሱም አ’ርጎሃል፤

    እናም ያጸናሃል፤

    ያጠነክርሃል።

    እንደ ቀድሞው ይመራሃል፤

    ይጠብቅሃል።

    አዎ ያጸናሃል፤

    ያጠነክርሃል።

(በተጨማሪም ሮም 8:32⁠፤ 14:8, 9⁠ን፣ ዕብ. 6:10⁠ን እና 1 ጴጥ. 2:9⁠ን ተመልከት።)