መዝሙር 40
የማን ንብረት ነን?
(ሮም 14:8)
-
1. ’ምትኖረው ለማን ነው?
ማንን ነው ’ምታመልከው?
ልትገዛለት የምትመርጠው፣
ጌታህ ’ሚሆነው እሱ ነው።
ለሁለት አማልክት
ልብን ከፍሎ በመስጠት፣
ሁለቱን መውደድ ስለማይቻል
መወሰን ይገባሃል።
-
2. ’ምትኖረው ለማን ነው?
ማንን ነው ’ምታመልከው?
አንደኛው እውነት፣ ሌላው ሐሰት
ናቸውና አንዱን ምረጥ።
ታማኝ የምትሆነው
ለዚህ ዓለም ቄሳር ነው?
ወይስ ለእውነተኛው አምላክህ
ዘወትር ትገዛለህ?
-
3. እኔ የምኖረው፣
ሁሌም የምታዘዘው፣
የተሳልኩትን ’ምፈጽመው
ሰማይ ላለው አምላኬ ነው።
በዋጋ ገዝቶኛል፤
ታማኝ ልሆን ይገባል።
መላ ሕይወቴን ሰጥቼዋለሁ፤
ስሙን አወድሳለሁ።
(በተጨማሪም ኢያሱ 24:15ን፣ መዝ. 116:14, 18ን እና 2 ጢሞ. 2:19ን ተመልከት።)