በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 64

በመከሩ ሥራ በደስታ መካፈል

በመከሩ ሥራ በደስታ መካፈል

(ማቴዎስ 13:1-23)

  1. 1. ያለነው በመከር ወራት ነው፤

    ይህ ለኛ ታላቅ ክብር ነው።

    መከሩ ለአጨዳ ደርሷል፤

    ለኛም ድርሻ ተሰጥቶናል።

    ሥራውን እየመራ ያለው

    ምሳሌያችን ኢየሱስ ነው።

    ያገኘነው መብት እጅግ ታላቅ ነው፤

    በደስታ እንፈጽመው።

  2. 2. ለአምላክ፣ ለሰው ያለን ፍቅር፣

    እንድንተጋ ግድ ይለናል።

    የመከር ሥራው አስቸኳይ ነው፤

    የመጨረሻው ቀን ቀርቧል።

    ከአምላክ ጋር አብረን ስንሠራ

    ወደር የለውም ደስታችን።

    አምላክ በሰጠን ሥራ ከጸናን

    በረከት እናገኛለን።

(በተጨማሪም ማቴ. 24:13⁠ን፣ 1 ቆሮ. 3:9⁠ን እና 2 ጢሞ. 4:2⁠ን ተመልከት።)