መዝሙር 71
የይሖዋ ሠራዊት ነን!
-
1. የአምላክ ሠራዊት ነን፤
’የሱስ ’ሚመራን።
ሰይጣን ቢቃወመንም
ፍርሃት አይሰማንም።
እንገፋለን ወደፊት፣
በታማኝነት።
አለን ጽኑ አቋም፤
ቅንጣት አንፈራም።
(አዝማች)
የአምላክ ሠራዊት ነን፣
ከ’የሱስ ጋር አንድ፤
መግዛት መጀመሩን
በደስታ ’ናውጅ።
-
2. ያምላክ አገልጋዮች ነን፤
እንፈልጋለን
የባዘኑ በጎችን፤
’ሚያለቅሱ፣ ’ሚያዝኑትን።
እንርዳቸው ቅኖችን
ሳንሰለች ሄደን።
እንጋብዛቸው ሁሌ፣
ወደ ጉባኤ።
(አዝማች)
የአምላክ ሠራዊት ነን፣
ከ’የሱስ ጋር አንድ፤
መግዛት መጀመሩን
በደስታ ’ናውጅ።
-
3. የአምላክ ሠራዊት ነን፤
እንዘምታለን
ትጥቃችንን አሟልተን፣
ቦታችንን ይዘን።
ቆራጥ አቋም ይኑረን፤
ጥንቁቆች እንሁን።
በአስቸጋሪም ወቅት፣
እንጽና በ’ውነት።
(አዝማች)
የአምላክ ሠራዊት ነን፣
ከ’የሱስ ጋር አንድ፤
መግዛት መጀመሩን
በደስታ ’ናውጅ።