በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 72

የመንግሥቱን እውነት ማሳወቅ

የመንግሥቱን እውነት ማሳወቅ

(የሐዋርያት ሥራ 20:20, 21)

  1. 1. ካሁን በፊት ባዝነን ነበር፤

    እውነተኛው መንገድ ጠፍቶን።

    አምላክ ግን አበራልን፤

    የመንግሥቱ እውነት ታየን።

    የሱን ፈቃድ ስላወቅን፣

    ላገዛዙ ታዛዦች ነን፤

    ዝናውን ’ናውጃለን፤

    ቅዱስ ስሙን እናሳውቃለን።

    በመንገድ ላይ፣ በየቤቱ፣

    ሁሉም ይድረሰው መልእክቱ።

    እናስተምር ለሰው ሁሉ፤

    ቃሉን አውቀው ነፃ ይውጡ።

    ምሥራቹን እናስፋፋ፤

    አምልኮውም ይታይ ልቆ።

    ባንድነት እናገልግል፤

    አምላክ በቃ ’ስኪለን ጊዜው አልቆ።

(በተጨማሪም ኢያሱ 9:9⁠ን፣ ኢሳ. 24:15⁠ን እና ዮሐ. 8:12, 32⁠ን ተመልከት።)