በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 87

ኑ! እረፍት አግኙ

ኑ! እረፍት አግኙ

(ዕብራውያን 10:24, 25)

  1. 1. የምንኖርበት ዓለም ብልሹ ነው፤

    ያምላክን መንገድ አያውቅም።

    አስተማማኝ መመሪያ ያስፈልጋል፤

    የራስ መንገድ አያዋጣም።

    ስብሰባዎቻችን ኃይል ያድሳሉ፤

    እምነት ያጠነክራሉ።

    ለመልካም ሥራ ያንቀሳቅሳሉ፤

    ለመበርታት ያስችላሉ።

    የይሖዋን ት’ዛዛት ቸል አንልም፤

    ፈቃዱን ማድረግ ’ንሻለን።

    ከስብሰባዎች መመሪያ ይገኛል፤

    ለ’ውነት ያለን ፍቅርም ያድጋል።

  2. 2. ይሖዋ ያውቃል የሚያስፈልገንን፤

    ምክሮቹን መስማት አለብን።

    ለስብሰባዎች ጊዜ መግዛታችን፣

    ያሳያል ጥበብ እንዳለን።

    የተሾሙ ወንዶች ’ሚያስተምሩን ቃል

    ያነሳሳናል ለተግባር።

    የወንድሞች ድጋፍ አይለየንም፤

    ብቻችንን አይደለንም።

    ለመኖር ከፈለግን ባዲስ ዓለም፣

    ስብሰባ መሄድ አንተውም።

    በስብሰባዎች ላይ እንማራለን፣

    ባምላክ ጥበብ መመራትን።

(በተጨማሪም መዝ. 37:18⁠፤ 140:1⁠ን፣ ምሳሌ 18:1⁠ን፣ ኤፌ. 5:16⁠ን እና ያዕ. 3:17⁠ን ተመልከት።)