መዝሙር 97
የአምላክ ቃል ሕይወት ነው
(ማቴዎስ 4:4)
-
1. ሕይወታችን የተመካው
በአምላክ ቃል ላይ ነው።
ሰው በምግብ ብቻ ’ይኖርም፤
ያምላክ ቃል ሕይወት ነው።
ሰላም፣ እርካታ ሰጥቶናል፤
ተስፋችን ለምልሟል።
(አዝማች)
ሰው በምግብ ብቻ ’ይኖርም፤
ያምላክ ቃል ሕይወት ነው።
በየ’ለቱ እናንብበው፤
ያምላክ ቃል ሕይወት ነው።
-
2. በቃሉ ውስጥ ያለው ታሪክ
ነው ልብ የሚማርክ።
የ’ምነት ምሳሌ ’ሚሆኑ
ብዙ ሰዎች አሉ።
ታሪካቸው ያጸናናል፤
ያበረታታናል።
(አዝማች)
ሰው በምግብ ብቻ ’ይኖርም፤
ያምላክ ቃል ሕይወት ነው።
በየ’ለቱ እናንብበው፤
ያምላክ ቃል ሕይወት ነው።
-
3. የአምላክ ቃል ያጽናናናል፤
ተስፋ ይሰጠናል።
ጥበበኞች ያደርገናል፤
ማስተዋል ሰጥቶናል።
በልባችን እናኑረው፤
በ’ርግጥም ሀብት ነው።
(አዝማች)
ሰው በምግብ ብቻ ’ይኖርም፤
ያምላክ ቃል ሕይወት ነው።
በየ’ለቱ እናንብበው፤
ያምላክ ቃል ሕይወት ነው።