መዝሙር 99
እልፍ አእላፋት ወንድሞች
-
1. እልፍ አእላፋት ወንድሞች፣
እጅግ ብዙ ሰዎች፣
ታማኝ ምሥክር ናቸው
ጸንተው ባቋማቸው።
እልፍ አእላፍ ሆነናል፤
በቁጥር በዝተናል።
ብሔር፣ ቋንቋ፣ ነገድ ሳይለየን
ያህን ’ናከብራለን።
-
2. እልፍ አእላፋት ወንድሞች፣
ሁሌም እንሰብካለን፤
ምሥራች ’ናበስራለን፣
በየቦታው ሄደን።
መመሥከር አናቆምም፣
ድካም ቢሰማንም፤
ኢየሱስ ለዛሉ ሰላምን፣
ይሰጣል እፎይታን።
-
3. እልፍ አእላፍ ወንድሞችን፣
አምላክ ይጠብቃል፤
ቀን ከሌት በመቅደሱ
ያገለግሉታል።
እልፍ አእላፍ ሆነናል፤
እንመሠክራለን፤
በምድራዊው አደባባይ ላይ
ከሱ ጋ ’ንሠራለን።