በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 106

ፍቅርን ማዳበር

ፍቅርን ማዳበር

(1 ቆሮንቶስ 13:1-8)

  1. 1. ወደ አምላክ እንጸልያለን፤

    ባሕርያቱን እንዲያላብሰን።

    በተለይ ከሁሉም ’ሚልቀው፣

    የመንፈሱ ውጤት ፍቅር ነው።

    ችሎታ፣ ጥበብ፣ ድፍረት ኖሮን፣

    ፍቅር ከሌለን ግን ከንቱ ነን።

    አምላክ እንዲረዳን ከጸለይን

    ታማኝ ፍቅር እናሳያለን።

  2. 2. ፍቅር አይሰስትም፣ ለጋስ ነው፤

    ስለ ሌሎች ነው የሚያስበው።

    ፍቅር በደልን ችሎ ያልፋል፤

    ታጋሽ ነው፤ ከልብ ይቅር ይላል።

    እንችላለን ችግር፣ መከራ፣

    ፍቅራችን ከሆነ ጠንካራ።

    ምንም ዓይነት ችግር ቢገጥመን፣

    ፍቅር አይከስምም ያልፋል ሁሉን።

(በተጨማሪም ዮሐ. 21:17⁠ን፣ 1 ቆሮ. 13:13⁠ን እና ገላ. 6:2⁠ን ተመልከት።)