በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 108

የአምላክ ታማኝ ፍቅር

የአምላክ ታማኝ ፍቅር

(ኢሳይያስ 55:1-3)

  1. 1. ይሖዋ ፍቅር ነው፤

    ጥሩነቱ ወደር የለው።

    ልጁን ለኛ ሲል ልኮታል፤

    ቤዛ እንዲሆን ሰጥቶናል።

    ስለወደደን አዳነን፤

    ከኃጢያት፣ ከሞት ታደገን።

    (አዝማች)

    እናንት የተጠማችሁ፣

    ወደ ሕይወት ውኃ ኑ።

    ያምላካችንን ፍቅር፣

    ጥሩነት ቅመሱ።

  2. 2. ይሖዋ ፍቅር ነው፤

    ሥራው ለዚህ ምሥክር ነው።

    አሳይቷል ታላቅ ፍቅሩን፣

    ሰማይ ላይ በማንገሥ ልጁን።

    ያምላክ መንግሥት ተቋቁሟል፤

    የገባው ቃል ይፈጸማል።

    (አዝማች)

    እናንት የተጠማችሁ፣

    ወደ ሕይወት ውኃ ኑ።

    ያምላካችንን ፍቅር፣

    ጥሩነት ቅመሱ።

  3. 3. ይሖዋ ፍቅር ነው፤

    እኛም እሱን እንምሰለው።

    ቅኖችን እናስተምራቸው፤

    መንገዱን እናሳያቸው።

    ለሰዎች እንስበክ ቃሉን፤

    እንንገራቸው መል’ክቱን።

    (አዝማች)

    እናንት የተጠማችሁ፣

    ወደ ሕይወት ውኃ ኑ።

    ያምላካችንን ፍቅር፣

    ጥሩነት ቅመሱ።

(በተጨማሪም መዝ. 33:5⁠፤ 57:10⁠ን እና ኤፌ. 1:7⁠ን ተመልከት።)