መዝሙር 115
አምላክ ላሳየን ትዕግሥት አመስጋኝ መሆን
-
1. አምላካችን፣ ታላቅ ነው ኃይልህ፤
ጽድቅን እጅግ ትወዳለህ።
ግን በምድር ክፋት ነግሷል፤
ልባችንም በጣም አዝኗል።
አትዘገይም፣ ለሰው ባይመስልም፤
ክፋት ይጠፋል፤ ጊዜው ቀርቧል።
(አዝማች)
አንተን ተስፋ ’ናደርጋለን፤
ስምህንም እናውጃለን።
-
2. እናውቃለን ሺህ ዓመት ላንተ፤
እንዳንድ ቀን እንደሆነ።
ታላቁ ቀንህ ይመጣል፤
አይዘገይም፣ ጊዜው ቀርቧል።
ኃጢያትን ሁሉ ብትጠላም፣
ሰው ሲመለስ ግን ደስ ይልሃል።
(አዝማች)
አንተን ተስፋ ’ናደርጋለን፤
ስምህንም እናውጃለን።
(በተጨማሪም ነህ. 9:30ን፣ ሉቃስ 15:7ን እና 2 ጴጥ. 3:8, 9ን ተመልከት።)