በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 125

“መሐሪዎች ደስተኞች ናቸው”

“መሐሪዎች ደስተኞች ናቸው”

(ማቴዎስ 5:7)

  1. 1. አምላካችን መሐሪ ነው፤

    በደስታ ነው የሚምረው።

    ለጋስ ነው፤ መስጠት ይወዳል፤

    ሕዝቦቹን ይንከባከባል።

    ይቅር ባይ አምላክ ነው እሱ፤

    ኃጢያተኞች ሲመለሱ።

    አፈር እንደሆንን ያውቃል፤

    ደግ አምላክ ነው፤ ይምረናል።

  2. 2. በፈጸምነው ኃጢያት ምክንያት

    ስንጠይቅ ያምላክን ምሕረት፣

    ጌታችን እንዳስተማረን

    በጸሎት ’ንማጸናለን፦

    ‘ሌሎችን ይቅር እንዳልን

    አምላክ ሆይ፣ እኛንም ማረን።’

    ከልባችን ይቅር ማለት

    ይሰጠናል ሰላም፣ እረፍት።

  3. 3. ለሰዎች እናሳይ ምሕረት፤

    ለጋሶች እንሁን የእውነት።

    ምንም ብድራት ሳንጠብቅ

    ለሰዎች መልካም እናድርግ።

    አምላካችን ይህን አይቶ

    ይባርከናል አሟልቶ።

    መሐሪዎች ደስተኞች፣

    ናቸው በአምላክ ፊት ውቦች።

(በተጨማሪም ማቴ. 6:2-4, 12-14⁠ን ተመልከት።)