በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 132

አንድ ሆነናል

አንድ ሆነናል

(ዘፍጥረት 2:23, 24)

  1. 1. ያጥንቶቼ አጥንት ናት፤

    አምላክ የሰጠኝ፣ የኔ ’ምላት።

    ሥጋዋም አንድ ከሥጋዬ፤

    ሆነችኝ አጋሬ።

    አንድ ሆነናል፤ እንጓጓለን

    ያምላክን በረከት ለማግኘት።

    በጋብቻ ተጣምረናል፤

    ቤተሰብ ሆነናል።

    ይሖዋን ’ናገለግላለን።

    እሱን በመምሰል

    ጽኑ ፍቅር ይኑረን።

    መሐላችን ይሳካልን፤

    የደስታ ዘመን ይሁንልን።

    ይሖዋ በኛ ይከበር፤

    አንቺም ሁኚ የኔ ፍቅር።

(በተጨማሪም ዘፍ. 29:18⁠ን፣ መክ. 4:9, 10⁠ን እና 1 ቆሮ. 13:8⁠ን ተመልከት።)