በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 141

ሕይወት ተአምር ነው

ሕይወት ተአምር ነው

(መዝሙር 36:9)

  1. 1. ልጅ መወለዱ፣ ዝናብ መጣሉ፣

    የፀሐይ ደማቅ ጮራ፣ የ’ህል ዛላ፣

    ሁሉም የአምላክ ስጦታ ናቸው፤

    በሕይወት የኖርነው በሱ ተአምር ነው።

    (አዝማች)

    እንዴት ’ናመስግነው፣ ለዚህ ስጦታው?

    እሱን መውደድ፣ ስጦታውን ማክበር ብቻ ነው።

    በኛ ጥረት ቢሆን ጭራሽ አናገኘው፤

    ሕይወት ስጦታ ነው፤ ሕይወት ተአምር ነው።

  2. 2. እንደ ኢዮብ ሚስት ተስፋ ’ሚቆርጡ፣

    አምላክን ’ሚያማርሩ ሰዎች አሉ።

    እኛ ግን ጌታን ’ናወድሳለን፤

    በሕይወት እንድንኖር ስላደረገን።

    (አዝማች)

    እንዴት እናመስግን፣ ለዚህ ስጦታ?

    ሰዎችን ’ንውደዳቸው እንስጣቸው ቦታ።

    በኛ ጥረት ቢሆን ጭራሽ አናገኘው፤

    ሕይወት ስጦታ ነው፤ ሕይወት ተአምር ነው።

(በተጨማሪም ኢዮብ 2:9⁠ን፣ መዝ. 34:12⁠ን፣ መክ. 8:15⁠ን፣ ማቴ. 22:37-40⁠ን እና ሮም 6:23⁠ን ተመልከት።)