በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 142

ተስፋችንን አጥብቀን እንያዝ

ተስፋችንን አጥብቀን እንያዝ

(ዕብራውያን 6:18, 19)

  1. 1. የሰው ዘር በጨለማ ሲዳክር ኖሯል።

    ጥረቱም ነፋስን ማሳደድ ሆኗል።

    አንዱ ሌላውን ለማዳን አይችልም፣

    ኃጢያት ስላለባቸው ሁሉም።

    (አዝማች)

    ደስ ይበላችሁ፤ መንግሥቱ ቀርቧል!

    ጌታ ከፍርሃት ነፃ ያወጣናል።

    ክፋት ሁሉ በቅርቡ ይጠፋል፤

    ይህ ተስፋ መልሕቅ ሆኖ ያቆመናል።

  2. 2. “ያምላክ ቀን ቀርቧል!” ብሎ ማወጅ ይገባል፤

    “እስከ መቼ?” ብሎ መጮኽ ያበቃል!

    ፍጥረት ነፃ ይወጣል ከመቃተት፤

    ለአምላክ እንዘምር በግለት።

    (አዝማች)

    ደስ ይበላችሁ፤ መንግሥቱ ቀርቧል!

    ጌታ ከፍርሃት ነፃ ያወጣናል።

    ክፋት ሁሉ በቅርቡ ይጠፋል፤

    ይህ ተስፋ መልሕቅ ሆኖ ያቆመናል።

(በተጨማሪም መዝ. 27:14⁠ን፣ መክ. 1:14⁠ን፣ ኢዩ. 2:1⁠ን፣ ዕን. 1:2, 3⁠ን እና ሮም 8:22⁠ን ተመልከት።)