በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ሣጥን 2ሀ

የሕዝቅኤልን ትንቢቶች መረዳት

የሕዝቅኤልን ትንቢቶች መረዳት

ትንቢት ምንድን ነው?

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “መተንበይ” ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ግስ ናቫ ሲሆን በዋነኝነት የሚያመለክተው አንድን ከአምላክ የመጣ መልእክት፣ ፍርድ፣ የሥነ ምግባር ትምህርት ወይም ትእዛዝ ማወጅን ነው። በተጨማሪም በመለኮታዊ አመራር ስለ ወደፊቱ ጊዜ መናገርን ሊያመለክት ይችላል። የሕዝቅኤል ትንቢቶች እነዚህን ሁሉ መለኮታዊ መልእክቶች ያካተቱ ናቸው።—ሕዝ. 3:10, 11፤ 11:4-8፤ 14:6, 7፤ 37:9, 10፤ 38:1-4

የቀረቡበት መንገድ

  • ራእዮች

  • ምሳሌዎች

  • ትንቢታዊ ድራማዎች

የሕዝቅኤል መጽሐፍ ራእዮችን፣ ምሳሌዎችንና በድራማ መልክ የቀረቡ ትንቢታዊ መልእክቶችን አካቷል።

ፍጻሜያቸው

ሕዝቅኤል የተናገራቸው ትንቢቶች አንዳንድ ጊዜ ከአንድ በላይ ፍጻሜ አላቸው። ለምሳሌ፣ ንጹሕ አምልኮ መልሶ እንደሚቋቋም የሚናገሩት ትንቢቶች የአምላክ ሕዝቦች ወደ ተስፋይቱ ምድር በተመለሱበት ጊዜ በተወሰነ መጠን ፍጻሜ አግኝተዋል። ነገር ግን በዚህ መጽሐፍ ምዕራፍ 9 ላይ እንደተብራራው ከእነዚህ ትንቢቶች መካከል ብዙዎቹ በዛሬው ጊዜ ፍጻሜያቸውን ያገኙ ከመሆኑም በላይ ወደፊትም ተጨማሪ ፍጻሜ ይኖራቸዋል።

ቀደም ሲል፣ በሕዝቅኤል ትንቢት ውስጥ የተገለጹት ብዙ ነገሮች ትንቢታዊ ጥላነት እንዳላቸው አድርገን እናስብ ነበር። ይህ መጽሐፍ ግን በቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ በግልጽ የሰፈረ ሐሳብ ከሌለ በስተቀር የትኛውንም ሰው፣ ዕቃ፣ ቦታ ወይም ክንውን በተመለከተ ጥላነት እንዳለውና ዘመናዊ ፍጻሜ እንደሚኖረው የሚገልጽ ማብራሪያ አይሰጥም። * ከዚህ ይልቅ ብዙዎቹ የሕዝቅኤል ትንቢቶች ስለሚኖራቸው የላቀ ፍጻሜ ይናገራል። በተጨማሪም ከሕዝቅኤል መልእክትና በሕዝቅኤል መጽሐፍ ውስጥ ከተጠቀሱት ሰዎች፣ ቦታዎችና ክንውኖች ምን ትምህርት ልናገኝ እንደምንችል ያብራራል።

^ አን.12 በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ የተለያዩ ነገሮች ትንቢታዊ ጥላነት እንዳላቸው ከመግለጽ የምንቆጠብበትን ምክንያት በተመለከተ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት የመጋቢት 15, 2015 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 9-11 ከአን. 7-12⁠ን እንዲሁም በዚሁ መጽሔት ከገጽ 17-18 ላይ የሚገኘውን “የአንባቢያን ጥያቄዎች” የሚለውን ዓምድ ተመልከት።