በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ሣጥን 6ሀ

“የራስህን ፀጉርና ጢምህን ተላጭ”

“የራስህን ፀጉርና ጢምህን ተላጭ”

ሕዝቅኤል በኢየሩሳሌም ላይ በቅርቡ የሚፈጸሙ ክንውኖችን በትንቢታዊ ድራማ መልክ አሳየ

  • “ተላጭ”

    አይሁዳውያን ጥቃት ይሰነዘርባቸዋል እንዲሁም ተጠራርገው ይጠፋሉ

  • “መዝነውና ከፋፍለው”

    የይሖዋ ፍርድ በታሰበበትና ሥር ነቀል በሆነ መንገድ የሚፈጸም ይሆናል

  • ‘አቃጥለው’

    አንዳንዶች በከተማዋ ውስጥ ይሞታሉ

  • ‘ምታው’

    አንዳንዶች ከከተማዋ ውጭ ይገደላሉ

  • ‘በትነው’

    አንዳንዶች ከጥፋቱ ያመልጣሉ፤ ግን ሰላም አያገኙም

  • “ቋጥራቸው”

    አንዳንድ ግዞተኞች ወደ ኢየሩሳሌም ይመለሳሉ፤ ንጹሕ አምልኮም ሙሉ በሙሉ አይጠፋም