በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ሣጥን 7ሀ

በኢየሩሳሌም ዙሪያ የነበሩት ብሔራት

650-300 ዓ.ዓ. ገደማ

በኢየሩሳሌም ዙሪያ የነበሩት ብሔራት

የጊዜ ሰሌዳ (ዓ.ዓ.)

  1. 620፦ ባቢሎን ኢየሩሳሌምን ማስተዳደር ጀመረች።

    ናቡከደነጾር የኢየሩሳሌምን ንጉሥ ገባር ንጉሥ አደረገው

  2. 617፦ ባቢሎን የመጀመሪያዎቹን ምርኮኞች ወሰደች።

    ገዢዎች፣ ኃያላን ተዋጊዎችና የእጅ ጥበብ ባለሙያዎች ወደ ባቢሎን በምርኮ ተወሰዱ

  3. 607፦ ባቢሎን ኢየሩሳሌምን አጠፋች።

    ኢየሩሳሌምና ቤተ መቅደሷ ተቃጠሉ

  4. ከ607 በኋላ፦ በየብስ ላይ የሚገኘው የጢሮስ ክፍል።

    ናቡከደነጾር በጢሮስ ላይ ለ13 ዓመት የዘለቀ ጥቃት ሰነዘረ። በየብስ ላይ ያለውን የጢሮስ ክፍል ድል አደረገ፤ ደሴት ላይ የሚገኘው የከተማዋ ክፍል ግን አልተነካም

  5. 602፦ አሞንና ሞዓብ።

    ናቡከደነጾር አሞንንና ሞዓብን ወረረ

  6. 588፦ ባቢሎን ግብፅን ድል አደረገች።

    ናቡከደነጾር በ37ኛው የግዛት ዘመኑ ግብፅን ወረረ

  7. 332፦ ደሴት ላይ የምትገኘው የጢሮስ ከተማ።

    በታላቁ እስክንድር ይመራ የነበረው የግሪክ ሠራዊት ደሴት ላይ የምትገኘውን የጢሮስ ከተማ አወደመ

  8. 332 ወይም ከዚያ በፊት፦ ፍልስጤም።

    እስክንድር የፍልስጤም ዋና ከተማ የነበረችውን ጋዛን ድል አድርጎ ያዘ

በካርታው ላይ የተጠቀሱ ቦታዎች

  • ግሪክ

  • ታላቁ ባሕር

  • (ሜድትራንያን ባሕር)

  • ጢሮስ

  • ሲዶና

  • ጢሮስ

  • ሰማርያ

  • ኢየሩሳሌም

  • ጋዛ

  • ፍልስጤም

  • ግብፅ

  • ባቢሎን

  • አሞን

  • ሞዓብ

  • ኤዶም