በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ሣጥን 18ሀ

ይሖዋ ስለ መጪው ታላቅ ጦርነት የሰጠው ማስጠንቀቂያ

ይሖዋ ስለ መጪው ታላቅ ጦርነት የሰጠው ማስጠንቀቂያ

ይሖዋ እሱንና ሕዝቦቹን የሚቃወሙትን ሁሉ ጠራርጎ የሚያጠፋበት አንድ ታላቅ ጦርነት እንደሚመጣ የሚያስጠነቅቁ በርካታ ትንቢቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይገኛሉ። ከእነዚህ ትንቢቶች መካከል አንዳንዶቹ ከዚህ ቀጥሎ ተዘርዝረዋል። በእነዚህ ማስጠንቀቂያዎች መካከል ያለውን ተመሳሳይነት እንዲሁም ይሖዋ ሰዎች በሙሉ ማስጠንቀቂያውን ሰምተው እርምጃ የመውሰድ አጋጣሚ እንዲያገኙ ያደረገው እንዴት እንደሆነ ለማስተዋል ሞክር።

በጥንቷ እስራኤል ዘመን

ሕዝቅኤል፦ “‘በተራሮቼ ሁሉ፣ በጎግ ላይ ሰይፍ እጠራለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”—ሕዝ. 38:18-23

ኤርምያስ፦ “[ይሖዋ] ራሱ በሰዎች ሁሉ ላይ ይፈርዳል። ክፉዎችንም ለሰይፍ ይዳርጋል።”—ኤር. 25:31-33

ዳንኤል፦ “የሰማይ አምላክ ፈጽሞ የማይጠፋ መንግሥት ያቋቁማል። ይህም መንግሥት . . . እነዚህን መንግሥታት ሁሉ ያደቅቃል፤ ፈጽሞም ያጠፋቸዋል።”—ዳን. 2:44

በመጀመሪያው መቶ ዘመን ዓ.ም.

ኢየሱስ፦ “ከዓለም መጀመሪያ አንስቶ እስካሁን ድረስ ሆኖ የማያውቅ ዳግመኛም የማይሆን ታላቅ መከራ ይከሰታል።”—ማቴ. 24:21, 22

ጳውሎስ፦ “ኢየሱስ ከኃያላን መላእክቱ ጋር . . . አምላክን በማያውቁት . . . ላይ የበቀል እርምጃ ይወስዳል።”—2 ተሰ. 1:6-9

ጴጥሮስ፦ “የይሖዋ ቀን እንደ ሌባ ይመጣል፤ . . . ምድርና በላይዋ የተሠሩ ነገሮችም ይጋለጣሉ።”—2 ጴጥ. 3:10

ዮሐንስ፦ “[ኢየሱስ] ብሔራትን ይመታበት ዘንድ ከአፉ ረጅም ስለታም ሰይፍ ይወጣል።”—ራእይ 19:11-18

በዘመናችን

መጽሐፍ ቅዱስ ከየትኛውም መጽሐፍ ይበልጥ በብዛት የተተረጎመና የተሰራጨ መጽሐፍ ነው

በዘመናችን ያሉ የይሖዋ አገልጋዮች . . .

  • በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ጽሑፎችን በቢሊዮኖች በሚቆጠሩ ቅጂዎችና በመቶዎች በሚቆጠሩ ቋንቋዎች ያሰራጫሉ

  • በየዓመቱ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ሰዓት በስብከቱ ሥራ ያሳልፋሉ