በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ሣጥን 21ሀ

“መዋጮ አድርጋችሁ ለመስጠት የምትለዩት መሬት”

“መዋጮ አድርጋችሁ ለመስጠት የምትለዩት መሬት”

ሕዝቅኤል 48:8

እስቲ ከሕዝቅኤል ጋር ሆነን ይሖዋ የለየውን መሬት አንድ በአንድ ለመመልከት እንሞክር። ይህ መሬት አምስት ክፍሎች አሉት። እነዚህ ክፍሎች የትኞቹ ናቸው? ለምን ዓላማስ የሚያገለግሉ ነበሩ?

ሀ. ‘መዋጮ ተደርጎ የተሰጠው መሬት’

ለአስተዳደራዊ ሥራዎች የሚውል መሬት ሲሆን “የአስተዳደር ማዕከል” ተብሎ ይጠራል።

ሕዝ. 48:8

ለ. “በመዋጮ የተሰጠው መሬት በአጠቃላይ”

ለካህናቱ፣ ለሌዋውያኑና ለከተማዋ የተለየ መሬት ነው። በተጨማሪም የ12ቱም ነገዶች አባላት የሆኑ ሰዎች ይሖዋን ለማምለክና የአስተዳደር ዝግጅቱን ለመደገፍ ወደዚህ ቦታ ይመጣሉ።

ሕዝ. 48:20

ሐ. “የአለቃው ክልል”

“ይህ መሬት በእስራኤል ምድር የእሱ ርስት ይሆናል።” “ይህም የአለቃው ይሆናል።”

ሕዝ. 45:7, 8፤ 48:21, 22

መ. “መዋጮ ሆኖ የተሰጠ ቅዱስ ስፍራ”

ይህ ቦታ “ቅዱስ ድርሻ” ተብሎም ተጠርቷል። የላይኛው ክፍል ‘ለሌዋውያን’ የተመደበ “የተቀደሰ” ድርሻ ነው። መካከለኛው ክፍል “ለካህናቱ መዋጮ ሆኖ የሚሰጥ ቅዱስ ስፍራ” ነው። “ለቤቶቻቸው እንዲሁም ለመቅደሱ የሚሆን” ቦታ ነው።

ሕዝ. 45:1-5፤ 48:9-14

ሠ. “የቀረው ቦታ”

ይህ ቦታ “ለእስራኤል ቤት ሁሉ” የሚሆን ርስት ሲሆን ተራ ለሆነ የከተማዋ አገልግሎት ይኸውም “ለመኖሪያ ቤትና ለግጦሽ መሬት ይውላል።”

ሕዝ. 45:6፤ 48:15-19