ጥናት 3
ጥያቄዎችን መጠቀም
ማቴዎስ 16:13-16
ፍሬ ሐሳብ፦ አድማጮችህ ለመልእክቱ ጉጉት እንዲያድርባቸውና ተመስጠው እንዲከታተሉህ ለማድረግ፣ ነጥቡን አሳማኝ በሆነ መንገድ ለማስረዳት እንዲሁም ዋና ዋና ነጥቦችን ለማጉላት ጥያቄዎችን በተገቢው መንገድ ተጠቀም።
ይህን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?
-
አድማጮችህ ጉጉት እንዲያድርባቸውና ተመስጠው እንዲከታተሉህ አድርግ። አድማጮች ስለ ትምህርቱ ቆም ብለው እንዲያስቡ ወይም መልሱን ለማወቅ እንዲጓጉ የሚያደርጉ ጥያቄዎችን ተጠቀም።
-
ነጥቡን አሳማኝ በሆነ መንገድ አስረዳ። አድማጮች ትክክለኛው መደምደሚያ ላይ እንዲደርሱ የሚረዱ ጥያቄዎችን በማንሳት ትምህርቱን አሳማኝና ግልጽ በሆነ መንገድ አቅርብ።
-
ዋና ዋና ነጥቦችን አጉላ። የማወቅ ፍላጎት የሚቀሰቅሱ ጥያቄዎችን በመጠየቅ ቁልፍ ነጥቦችን ማስተዋወቅ ትችላለህ። አንድ አስፈላጊ ነጥብ ካብራራህ በኋላ ወይም ደግሞ ንግግርህን ስትደመድም የክለሳ ጥያቄዎችን ተጠቀም።