በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ጥናት 5

ጥርት ያለ ንባብ

ጥርት ያለ ንባብ

1 ጢሞቴዎስ 4:13

ፍሬ ሐሳብ፦ በጽሑፉ ላይ የሰፈረውን ነገር ምንም ሳትጨምርና ሳትቀንስ አንብብ።

ይህን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?

  • በሚገባ ተዘጋጅ። ጽሑፉ የተዘጋጀበትን ዓላማ ለመረዳት ጥረት አድርግ። በምታነብበት ጊዜ ቃላትን በተናጠል ከማንበብ ይልቅ የተወሰኑ ቃላትን አንድ ላይ ለማንበብ ሞክር። ቃላትንና ፊደላትን ላለመግደፍ ወይም አንዱን ቃል በሌላ ተክተህ ላለማንበብ ጥንቃቄ አድርግ። ሁሉንም ሥርዓተ ነጥቦች (ለምሳሌ ጥያቄ ምልክት፣ ነጠላ ሰረዝ ወይም ድርብ ሰረዝ) አስተውል።

  • እያንዳንዱን ቃል በትክክል ጥራ። አንድን ቃል እንዴት መጥራት እንዳለብህ ካላወቅክ መዝገበ ቃላት ተመልከት፣ በድምፅ የተቀዱ ጽሑፎችን አዳምጥ ወይም ጥሩ አንባቢ የሆነ ሰው እንዲረዳህ ጠይቅ።

  • ጥርት አድርገህ ተናገር። ቀና ብለህና አፍህን በደንብ ከፍተህ ቃላትን ጥርት ባለ መንገድ ለማንበብ ጥረት አድርግ። ቃላትን ሳትውጥ ወይም አንድ ላይ ሳትጨፈልቅ ግልጽ ሆኖ በሚሰማ መንገድ አንብብ።