በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ጥናት 6

የጥቅሱን ዓላማ ግልጽ ማድረግ

የጥቅሱን ዓላማ ግልጽ ማድረግ

ዮሐንስ 10:33-36

ፍሬ ሐሳብ፦ አንድን ጥቅስ ካነበብክ በኋላ ሳታብራራው ወደ ሌላ ነጥብ አትለፍ። አድማጮችህ ባነበብከው ጥቅስና እያብራራኸው ባለው ነጥብ መካከል ያለውን ዝምድና እንዲያስተውሉ እርዳቸው።

ይህን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?

  • ቁልፍ ቃላትን ለይተህ አውጣ። ጥቅስ ካነበብክ በኋላ ከዋናው ነጥብ ጋር በቀጥታ የሚዛመዱትን ቃላት አጉላ። እነዚህን ቃላት በመድገም ወይም ደግሞ አድማጮች ቁልፍ የሆኑትን ቃላት እንዲለዩ የሚረዳ ጥያቄ በማንሳት ይህን ማድረግ ትችላለህ።

  • ዋናውን ነጥብ ጎላ አድርገህ ግለጽ። አንድን ጥቅስ የምታነብበትን ዓላማ ተናግረህ ከነበረ ጥቅሱን ካነበብክ በኋላ ቁልፍ የሆኑት ቃላት፣ ጥቅሱ የተጠቀሰበትን ዓላማ የሚደግፉት እንዴት እንደሆነ አብራራ።

  • ጥቅሱ እንዴት ተግባራዊ እንደሚሆን ባልተወሳሰበ መንገድ አስረዳ። ከዋናው ነጥብ ጋር ብዙም ተያያዥነት የሌላቸውን ነጥቦች አታብራራ። አድማጮችህ ስለ ርዕሰ ጉዳዩ የሚያውቁትን ነገር ከግምት አስገባ፤ ከዚያም ጥቅሱ እንዴት ተግባራዊ እንደሚሆን ለማስረዳት ምን ያህል ማብራሪያ መስጠት እንዳለብህ ወስን።