በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ጥናት 15

በእርግጠኝነት መናገር

በእርግጠኝነት መናገር

1 ተሰሎንቄ 1:5

ፍሬ ሐሳብ፦ የምትናገረው ነገር ትክክለኛና በጣም አስፈላጊ መሆኑን ከልብህ እንደምታምን በሚያሳይ መንገድ ተናገር።

ይህን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?

  • በሚገባ ተዘጋጅ። ዋና ዋናዎቹ ነጥቦች ፍንትው ብለው እስኪታዩህ እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስ እነዚህን ሐሳቦች እንዴት እንደሚደግፍ በደንብ እስኪገባህ ድረስ ትምህርቱን አጥናው። ከዚያም ዋና ዋናዎቹን ነጥቦች እጥር ምጥን ባለ መንገድ ለማስቀመጥ ሞክር። ትምህርቱ አድማጮችህን እንዴት ሊጠቅም እንደሚችል አስብ። የመንፈስ ቅዱስን እርዳታ ለማግኘት ጸልይ።

  • ትምህርቱን ከልብህ እንደምታምንበት የሚያሳዩ ቃላትን ተጠቀም። በጽሑፉ ላይ የሰፈረውን ሐሳብ ቃል በቃል ከመድገም ይልቅ ሐሳቡን በራስህ አባባል ግለጸው። የምትናገረው ነገር እውነት መሆኑን እንደምታምን የሚያሳዩ አገላለጾችን ተጠቀም።

  • እርግጠኛ እንደሆንክ በሚያሳይ መንገድ ተናገር። ድምፅህ ጎላ ብሎ ሊሰማ ይገባል። በአካባቢያችሁ እንደ ነውር የማይቆጠር ከሆነ የአድማጮችህን ዓይን እያየህ ተናገር።