ጥናት 17
በቀላሉ የሚገባ
ይህን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?
-
ጥሩ ዝግጅት አድርግ። ትምህርቱን ቀላል በሆነ መንገድ እንዲሁም በራስህ አባባል ማቅረብ እንድትችል ርዕሰ ጉዳዩን በደንብ መረዳት ይኖርብሃል።
-
አጫጭር ዓረፍተ ነገሮችንና ያልተወሳሰቡ ሐረጎችን ተጠቀም። ረዘም ያሉ ዓረፍተ ነገሮችን መጠቀም የምትችል ቢሆንም ዋና ዋና ነጥቦችን ለማስተላለፍ እጥር ምጥን ያሉ ዓረፍተ ነገሮችንና ሐረጎችን መጠቀሙ የተሻለ ነው።
-
ያልተለመዱ ቃላትን ትርጉም አብራራ። በተቻለ መጠን፣ ያልተለመዱ ቃላትን ላለመጠቀም ጥረት አድርግ። አድማጮችህ የማያውቋቸውን ቃላት፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ ሰዎችን ወይም ጥንታዊ መለኪያዎችንና ልማዶችን የግድ መጥቀስ ካለብህ ተጨማሪ ማብራሪያ ስጥ።