በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ምዕራፍ 13

የሐሰት ሃይማኖቶች የአምላክን ስም ያሰደቡት እንዴት ነው?

የሐሰት ሃይማኖቶች የአምላክን ስም ያሰደቡት እንዴት ነው?

አምላክ ፍቅር ነው፤ ሆኖም እሱን እንደሚወክሉ የሚናገሩ ሃይማኖቶች በርካታ አስከፊ ድርጊቶችን ይፈጽማሉ። ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? በቀላል አነጋገር፣ ይህ ሊሆን የቻለው እነዚህ ሃይማኖቶች ሐሰት ስለሆኑ ነው፤ የሚያደርጉትና የሚናገሩት ነገር ሰዎች ስለ አምላክ የተሳሳተ ድምዳሜ ላይ እንዲደርሱ ያደርጋል። የሐሰት ሃይማኖቶች የአምላክን ስም የሚያሰድቡት እንዴት ነው? አምላክ ይህን ሲያይ ምን ይሰማዋል? ወደፊትስ ምን እርምጃ ይወስዳል?

1. የሐሰት ሃይማኖቶች የሚያስተምሩት ትምህርት አምላክን የሚያሰድበው እንዴት ነው?

የሐሰት ሃይማኖቶች “የአምላክን እውነት በሐሰት ለውጠዋል።” (ሮም 1:25) ለምሳሌ ያህል፣ ብዙ ሃይማኖቶች የአምላክ ስም ማን እንደሆነ ለተከታዮቻቸው አያስተምሩም። መጽሐፍ ቅዱስ ግን የአምላክን ስም መጠቀም አስፈላጊ እንደሆነ ይገልጻል። (ሮም 10:13, 14) አንዳንድ የሃይማኖት መሪዎች አንድ መጥፎ ነገር ሲከሰት አምላክ ያመጣው እንደሆነ ይናገራሉ። ሆኖም ይህ ውሸት ነው። አምላክ በምንም ዓይነት መጥፎ የሆነ ነገር አያደርግም። (ያዕቆብ 1:13⁠ን አንብብ።) የሚያሳዝነው፣ የሐሰት ሃይማኖቶች የሚያስተምሩት ውሸት ሰዎች ከአምላክ እንዲርቁ አድርጓል።

2. የሐሰት ሃይማኖቶች በድርጊታቸው አምላክን የሚያሰድቡት እንዴት ነው?

የሐሰት ሃይማኖት መሪዎች ሰዎችን የሚይዙበት መንገድ ይሖዋ ሰዎችን ከሚይዝበት መንገድ ፈጽሞ የተለየ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ የሐሰት ሃይማኖት ‘ኃጢአት እስከ ሰማይ ድረስ እንደተቆለለ’ ይናገራል። (ራእይ 18:5) በመቶዎች ለሚቆጠሩ ዓመታት፣ ሃይማኖቶች ፖለቲካ ውስጥ ሲገቡና ጦርነቶችን ሲደግፉ ቆይተዋል፤ በተጨማሪም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ፣ ስፍር ቁጥር ለሌላቸው ሰዎች ሞት ምክንያት ሆነዋል። አንዳንድ የሃይማኖት መሪዎች የተንደላቀቀ ሕይወት ለመኖር ሲሉ ተከታዮቻቸውን ገንዘብ እንዲያመጡ ይጠይቃሉ። እንዲህ ያሉት ድርጊቶች እነዚህ ሃይማኖቶች አምላክን ሊወክሉ ቀርቶ ጨርሶ እንደማያውቁት ያሳያሉ።—1 ዮሐንስ 4:8⁠ን አንብብ።

3. አምላክ ስለ ሐሰት ሃይማኖቶች ምን ይሰማዋል?

አንተ የሐሰት ሃይማኖቶች የሚያደርጉትን ነገር ስታይ የምታዝን ከሆነ ይሖዋስ ምን የሚሰማው ይመስልሃል? ይሖዋ ሰዎችን የሚወድ ቢሆንም የእሱን ስም የሚያሰድቡትንና ተከታዮቻቸውን የሚጨቁኑትን የሐሰት ሃይማኖት መሪዎች ማየት ያስቆጣዋል። የሐሰት ሃይማኖቶች እንደሚጠፉና ‘ዳግመኛ እንደማይገኙ’ ቃል ገብቷል። (ራእይ 18:21) በቅርቡ አምላክ የሐሰት ሃይማኖቶችን በሙሉ ያጠፋል።—ራእይ 18:8

ጠለቅ ያለ ጥናት

አምላክ ስለ ሐሰት ሃይማኖት ምን እንደሚሰማው በስፋት እንመለከታለን። እንዲሁም የሐሰት ሃይማኖቶች ያደረጓቸውን ሌሎች ነገሮችና የእነሱ ድርጊት ይሖዋን ከማወቅ ወደኋላ ሊያደርግህ የማይገባው ለምን እንደሆነ እንመረምራለን።

4. አምላክ የማይቀበላቸው ሃይማኖቶች አሉ

ብዙ ሰዎች ሃይማኖቶችን የሚመለከቷቸው ወደ አምላክ እንደሚያደርሱ የተለያዩ መንገዶች አድርገው ነው። ሆኖም ይህ እውነት ነው? ማቴዎስ 7:13, 14ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • መጽሐፍ ቅዱስ ወደ ሕይወት የሚወስደውን መንገድ በተመለከተ ምን ይላል?

ቪዲዮውን ተመልከቱ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ ሁሉንም ሃይማኖቶች እንደሚቀበል ያስተምራል?

5. የሐሰት ሃይማኖቶች አፍቃሪ የሆነውን አምላክ ባሕርይ አያንጸባርቁም

ሃይማኖቶች በብዙ መንገዶች ከአምላክ የተለየ አቋም እንዳላቸው አሳይተዋል። አንዱ መንገድ በጦርነት ያደረጉት ተሳትፎ ነው። ለዚህ የሚሆን ምሳሌ ለማየት ቪዲዮውን ተመልከቱ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ላይ በርካታ አብያተ ክርስቲያናት ምን አቋም ነበራቸው?

  • ስለያዙት አቋም ምን ይሰማሃል?

ዮሐንስ 13:34, 35ን እንዲሁም 17:16ን አንብቡ። ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • ሃይማኖቶች በጦርነት ሲሳተፉ ይሖዋ ምን የሚሰማው ይመስልሃል?

  • የሐሰት ሃይማኖቶች በዓለማችን ላይ ለሚፈጸሙት በርካታ መጥፎ ነገሮች ተጠያቂ ናቸው። ሃይማኖቶች እንደ አምላክ አፍቃሪ እንዳልሆኑ የሚያሳዩ ምን ማስረጃዎችን ተመልክተሃል?

የሐሰት ሃይማኖቶች አፍቃሪ የሆነውን አምላክ ባሕርይ አያንጸባርቁም

6. አምላክ ሰዎችን ከሐሰት ሃይማኖት ባርነት ነፃ ማውጣት ይፈልጋል

ራእይ 18:4ን አንብቡ፤ a ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • አምላክ በሐሰት ሃይማኖት የተታለሉ ሰዎችን ማዳን እንደሚፈልግ ማወቅህ ምን እንዲሰማህ ያደርጋል?

7. ስለ እውነተኛው አምላክ መማርህን ቀጥል

የሐሰት ሃይማኖቶች ስለ አምላክ መጥፎ አመለካከት እንዲያድርብህ ሊያደርጉ ይገባል? አባቱ የሚሰጠውን ጥሩ ምክር ችላ ያለን ልጅ እንደ ምሳሌ እንውሰድ። ልጁ ከቤት ወጥቶ መጥፎ ሕይወት መኖር ይጀምራል። አባትየው ልጁ የሚያደርጋቸውን ነገሮች አይደግፍም። ታዲያ ይህ ዓመፀኛ ልጅ በሕይወቱ ለሚያደርጋቸው ነገሮች አባትየውን መውቀስ ተገቢ ይመስልሃል?

  • የሐሰት ሃይማኖቶች ለሚያደርጉት ነገር ይሖዋን መውቀስና በዚህ የተነሳ ስለ እሱ መማርህን ማቆም ተገቢ ይመስልሃል?

አንዳንዶች እንዲህ ይላሉ፦ “ስለ ሃይማኖት ማውራት አልፈልግም፤ ምክንያቱም ሁሉም ሃይማኖቶች አስመሳዮች ናቸው።”

  • አንተስ እንደዚህ ይሰማሃል?

  • የሐሰት ሃይማኖቶች የሚያደርጉት ነገር ስለ ይሖዋ መጥፎ አመለካከት እንዲያድርብን ሊያደርግ አይገባም የምንለው ለምንድን ነው?

ማጠቃለያ

የሐሰት ሃይማኖቶች፣ በሚያስተምሩት የሐሰት ትምህርትና በሚፈጽሙት አስከፊ ድርጊት የአምላክን ስም አሰድበዋል። አምላክ የሐሰት ሃይማኖቶችን ያጠፋል።

ክለሳ

  • የሐሰት ሃይማኖቶች ስለሚያስተምሩት ትምህርትና ስለሚፈጽሙት ድርጊት ምን ይሰማሃል?

  • ይሖዋ የሐሰት ሃይማኖቶችን በተመለከተ ምን ይሰማዋል?

  • አምላክ ወደፊት በሐሰት ሃይማኖቶች ላይ ምን እርምጃ ይወስዳል?

ግብ

ምርምር አድርግ

አብዛኞቹ ሃይማኖቶች አምላክን የሚያሳዝኑት በየትኞቹ ሁለት መንገዶች ነው?

“ሁሉም ሃይማኖቶች አንድ ናቸው? ሁሉም ወደ አምላክ ያደርሳሉ?” (ድረ ገጻችን ላይ የወጣ ርዕስ)

ይሖዋ ከሌሎች ጋር ሆነን በአንድነት እንድናመልከው የሚፈልገው ለምንድን ነው?

“የአንድ ሃይማኖት አባል መሆን የግድ አስፈላጊ ነው?” (ድረ ገጻችን ላይ የወጣ ርዕስ)

አንድ ቄስ በሃይማኖቱ ውስጥ የሚያየው ነገር ይረብሸው ነበር። ሆኖም ይህ ስለ አምላክ እውነቱን ለማወቅ ጥረት ከማድረግ አላገደውም።

“አንድ ቄስ ይከተለው የነበረውን ሃይማኖት የተወው ለምንድን ነው?” (ንቁ! የካቲት 2015)

ለበርካታ ዘመናት የሐሰት ሃይማኖቶች፣ አምላክ ሊቀረብ የማይችልና ጨካኝ እንዲመስል የሚያደርጉ ትምህርቶች ሲያስተምሩ ቆይተዋል። ከእነዚህ ውሸቶች መካከል ሦስቱን በተመለከተ እውነታው ምንድን ነው?

“አምላክን መውደድ ከባድ እንዲሆን ያደረጉ ውሸቶች” (መጠበቂያ ግንብ ኅዳር 1, 2013)

a የራእይ መጽሐፍ የሐሰት ሃይማኖቶችን ታላቂቱ ባቢሎን በተባለች ሴት የሚመስላቸው ለምን እንደሆነ ለማወቅ ተጨማሪ ሐሳብ 1⁠ን ተመልከት።