በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ምዕራፍ 28

ይሖዋና ኢየሱስ ላደረጉልህ ነገር አድናቆት እንዳለህ አሳይ

ይሖዋና ኢየሱስ ላደረጉልህ ነገር አድናቆት እንዳለህ አሳይ

አንድ ጓደኛህ ጥሩ ስጦታ ቢሰጥህ ምን ይሰማሃል? በጣም እንደምትደሰትና ለስጦታው ያለህን አድናቆት ለጓደኛህ ማሳየት እንደምትፈልግ የታወቀ ነው። ይሖዋና ኢየሱስ ከሁሉ የላቀ ስጦታ ሰጥተውናል። ይህ ስጦታ ምንድን ነው? ለዚህ ስጦታ አድናቆት እንዳለን ማሳየት የምንችለውስ እንዴት ነው?

1. አምላክና ክርስቶስ ላደረጉልን ነገር አድናቆት እንዳለን የምናሳይበት አንዱ መንገድ ምንድን ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ‘በኢየሱስ የሚያምን ሁሉ’ የዘላለም ሕይወት እንደሚያገኝ ይናገራል። (ዮሐንስ 3:16 የግርጌ ማስታወሻ) በኢየሱስ እንደምናምን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው? ‘በኢየሱስ አምናለሁ’ ብሎ መናገር ብቻ በቂ አይደለም። ድርጊታችንም ሆነ በሕይወታችን የምናደርገው ምርጫ በኢየሱስ እንደምናምን የሚያሳይ ሊሆን ይገባል። (ያዕቆብ 2:17) በቃልም ሆነ በድርጊት እምነታችንን ስናሳይ ከኢየሱስና ከአባቱ ከይሖዋ ጋር ያለን ወዳጅነት ይጠናከራል።—ዮሐንስ 14:21⁠ን አንብብ።

2. ይሖዋና ኢየሱስ ላደረጉልን ነገር አድናቆታችንን ለማሳየት የሚያስችለን የትኛው ልዩ ዝግጅት ነው?

ኢየሱስ፣ ከመሞቱ በፊት በነበረው ምሽት ላይ ተከታዮቹ ለቤዛው ያላቸውን አድናቆት ማሳየት የሚችሉበትን ሌላ መንገድ ተናግሯል። መጽሐፍ ቅዱስ “የጌታ ራት” በማለት የሚጠራውን ልዩ በዓል አቋቁሟል፤ ይህ በዓል የክርስቶስ ሞት መታሰቢያ ተብሎም ይታወቃል። (1 ቆሮንቶስ 11:20) ኢየሱስ ይህን በዓል ያቋቋመው ሐዋርያቱና ከእነሱ በኋላ የሚመጡት እውነተኛ ክርስቲያኖች በሙሉ እሱ ለእኛ ሲል ሕይወቱን መስጠቱን እንዲያስታውሱ ነው። ኢየሱስ ይህን በዓል አስመልክቶ “ይህን ሁልጊዜ ለመታሰቢያዬ አድርጉት” የሚል ትእዛዝ ሰጥቷል። (ሉቃስ 22:19) በመታሰቢያው በዓል ላይ ስትገኝ ይሖዋና ኢየሱስ ለሰው ልጆች ላሳዩት ጥልቅ ፍቅር ያለህን አድናቆት ታሳያለህ።

ጠለቅ ያለ ጥናት

ይሖዋና ኢየሱስ ላሳዩት ጥልቅ ፍቅር አድናቆትህን ማሳየት የምትችልባቸውን ተጨማሪ መንገዶች እንመለከታለን። እንዲሁም የክርስቶስን ሞት መታሰቢያ ማክበር አስፈላጊ የሆነው ለምን እንደሆነ እናያለን።

3. አድናቆት ለተግባር ያነሳሳል

ውኃ ውስጥ ልትሰጥም ስትል አንድ ሰው አዳነህ እንበል። ይህ ሰው ያደረገልህን ነገር ትረሳዋለህ? ወይስ ላደረገልህ ነገር አድናቆትህን ለመግለጽ ትሞክራለህ?

የዘላለም ሕይወት የማግኘት አጋጣሚ የተከፈተልን በይሖዋ ደግነት ነው። አንደኛ ዮሐንስ 4:8-10ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • የኢየሱስ መሥዋዕት ልዩ ስጦታ ነው የምንለው ለምንድን ነው?

  • ይሖዋና ኢየሱስ ስላደረጉልህ ነገር ምን ይሰማሃል?

ይሖዋና ኢየሱስ ላደረጉልን ነገር አድናቆታችንን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው? ሁለተኛ ቆሮንቶስ 5:15ን እንዲሁም 1 ዮሐንስ 4:11⁠ን እና 5:3ን አንብቡ። እያንዳንዱን ጥቅስ ካነበባችሁ በኋላ በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • በዚህ ጥቅስ መሠረት አድናቆታችንን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?

4. ኢየሱስን ምሰል

አድናቆታችንን ማሳየት የምንችልበት ሌላው መንገድ ኢየሱስን መምሰል ነው። አንደኛ ጴጥሮስ 2:21ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • የኢየሱስን ፈለግ በጥብቅ መከተል የምትችለው በየትኞቹ መንገዶች ነው?

5. የክርስቶስን ሞት መታሰቢያ አክብር

ለመጀመሪያ ጊዜ የጌታ ራት ሲከበር የነበረውን ሁኔታ ለመመልከት ሉቃስ 22:14, 19, 20ን አንብቡ። ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • በጌታ ራት ላይ ምን ነገሮች ተከናውነዋል?

  • ቂጣውና የወይን ጠጁ ምን ያመለክታሉ?—ቁጥር 19 እና 20⁠ን ተመልከት።

ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ የጌታ ራትን በዓመት አንድ ጊዜ እሱ በሞተበት ዕለት እንዲያከብሩ አዟል። በመሆኑም የይሖዋ ምሥክሮች ኢየሱስ ባዘዘው መንገድ የሞቱን መታሰቢያ ለማክበር በየዓመቱ ይሰበሰባሉ። ትልቅ ቦታ ስለሚሰጠው ስለዚህ ስብሰባ ለማወቅ ቪዲዮውን ተመልከቱ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • በመታሰቢያው በዓል ላይ ምን ነገሮች ይከናወናሉ?

ቂጣውና የወይን ጠጁ ምሳሌያዊ ትርጉም አላቸው። ቂጣው ኢየሱስ ለእኛ ሲል መሥዋዕት ያደረገውን ፍጹም ሰብዓዊ አካሉን ያመለክታል። ወይን ጠጁ ደግሞ ደሙን ያመለክታል

አንዳንዶች እንዲህ ይላሉ፦ “ለመዳን የሚያስፈልገው በኢየሱስ ማመን ብቻ ነው።”

  • ዮሐንስ 3:16⁠ን እና ያዕቆብ 2:17⁠ን ተጠቅመህ እምነት ብቻውን በቂ እንዳልሆነ ማስረዳት የምትችለው እንዴት ነው?

ማጠቃለያ

በኢየሱስ እንደምናምን በተግባር በማሳየትና የሞቱን መታሰቢያ በማክበር ኢየሱስ ላደረገልን ነገር አድናቆታችንን ማሳየት እንችላለን።

ክለሳ

  • በኢየሱስ እንደምናምን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?

  • ይሖዋና ኢየሱስ ላደረጉልህ ነገር አድናቆትህን ለማሳየት ያሰብከው በምን መንገድ ነው?

  • የክርስቶስን ሞት መታሰቢያ ማክበር በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

ግብ

ምርምር አድርግ

ክርስቶስ እንደሞተልን ማወቃችን ምን ለማድረግ ያነሳሳናል?

በሥጋው ይሖዋን አክብሯል (9:28)

እምነት ምንድን ነው? እምነት እንዳለን ማሳየት የምንችለውስ እንዴት ነው?

“ይሖዋ በገባው ቃል ላይ እምነት እንዳላችሁ በተግባር አሳዩ” (መጠበቂያ ግንብ ጥቅምት 2016)

“ንጹሕ እንደሆንኩና ትርጉም ያለው ሕይወት መምራት እንደጀመርኩ ይሰማኛል” የሚል ርዕስ ባለው የሕይወት ታሪክ ላይ አንዲት ሴት ስለ ክርስቶስ መሥዋዕት ማወቋ ሕይወቷን የለወጠው እንዴት እንደሆነ አንብብ።

“መጽሐፍ ቅዱስ የሰዎችን ሕይወት ይለውጣል” (መጠበቂያ ግንብ ነሐሴ 1, 2011)

በመታሰቢያው በዓል ላይ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ከቂጣው የሚበሉትና ከወይን ጠጁ የሚጠጡት ለምንድን ነው?

“የይሖዋ ምሥክሮች የጌታ ራትን የሚያከብሩበት መንገድ ከሌሎች ሃይማኖቶች የተለየ የሆነው ለምንድን ነው?” (ድረ ገጻችን ላይ የወጣ ርዕስ)