በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ምዕራፍ 45

ገለልተኛ መሆን ማለት ምን ማለት ነው?

ገለልተኛ መሆን ማለት ምን ማለት ነው?

ኢየሱስ ተከታዮቹ “የዓለም ክፍል” መሆን እንደሌለባቸው አስተምሯል። (ዮሐንስ 15:19) ይህም ገለልተኛ መሆንን ማለትም በዓለም የፖለቲካ ጉዳዮችና ጦርነቶች ላይ የትኛውንም ወገን አለመደገፍን ይጨምራል። እንደ እውነቱ ከሆነ ገለልተኛ መሆን ቀላል የማይሆንበት ጊዜ አለ። በዚህ አቋማችን ምክንያት ሰዎች ሊያሾፉብን ይችላሉ። ታዲያ ምንጊዜም ገለልተኛ በመሆን ለይሖዋ አምላክ ታማኝ እንደሆንን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?

1. እውነተኛ ክርስቲያኖች ለዓለም መንግሥታት ምን አመለካከት አላቸው?

ክርስቲያኖች መንግሥትን ያከብራሉ። ኢየሱስ እንዳለው ‘የቄሳር የሆነውን ለቄሳር ለመስጠት’ ማለትም የአገሪቱን ሕጎች ለመታዘዝ ጥረት እናደርጋለን፤ ለምሳሌ ቀረጥ እንድንከፍል የሚያዝዙ ሕጎችን እንጠብቃለን። (ማርቆስ 12:17) መጽሐፍ ቅዱስ የዓለም መንግሥታት እየገዙ ያሉት ይሖዋ እንዲገዙ ስለፈቀደላቸው እንደሆነ ያስተምራል። (ሮም 13:1) በመሆኑም መንግሥታት ያላቸው ሥልጣን ከአምላክ አንጻር ሲታይ አነስተኛ ወይም የተገደበ መሆኑን እንገነዘባለን። የሰው ልጆችን ችግሮች መፍታት የሚችለው አምላክና እሱ በሰማይ ያቋቋመው መንግሥት ብቻ እንደሆነ እናምናለን።

2. ገለልተኛ መሆናችንን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?

ልክ እንደ ኢየሱስ ሁሉ እኛም ፖለቲካ ውስጥ አንገባም። ኢየሱስ ምድር ላይ ሳለ ሕዝቡ እሱ የፈጸመውን ተአምር አይተው ሊያነግሡት በሞከሩ ጊዜ ፈቃደኛ አልሆነም። (ዮሐንስ 6:15) ለምን? ምክንያቱም በኋላ ላይ እንደተናገረው ‘መንግሥቱ የዚህ ዓለም ክፍል አይደለም።’ (ዮሐንስ 18:36) እኛም የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት እንደመሆናችን መጠን ገለልተኛ መሆናችንን በተለያዩ መንገዶች እናሳያለን። ለምሳሌ ያህል፣ በጦርነት አንካፈልም። (ሚክያስ 4:3⁠ን አንብብ።) እንደ ባንዲራ ያሉ ብሔራዊ ዓርማዎችን የምናከብር ቢሆንም ለአምላክ የምንሰጠውን ዓይነት ክብር አንሰጣቸውም። (1 ዮሐንስ 5:21) በተጨማሪም የትኛውንም የፖለቲካ ፓርቲ ወይም የፓርቲውን ዕጩ አንደግፍም ወይም አንቃወምም። በእነዚህና በሌሎች መንገዶች ለአምላክ መንግሥት ሙሉ በሙሉ ታማኝ እንደሆንን እናሳያለን።

ጠለቅ ያለ ጥናት

የገለልተኝነት አቋምን ሊፈትኑ የሚችሉ ሁኔታዎችን እንመለከታለን፤ በተጨማሪም ይሖዋን የሚያስደስቱ ውሳኔዎችን ማድረግ የምትችለው እንዴት እንደሆነ እንመረምራለን።

3. እውነተኛ ክርስቲያኖች ገለልተኞች ናቸው

ኢየሱስና ተከታዮቹ ጥሩ ምሳሌ ትተውልናል። ሮም 13:1, 5-7ን እንዲሁም 1 ጴጥሮስ 2:13, 14ን አንብቡ። ከዚያም ቪዲዮውን ተመልከቱና በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • ባለሥልጣናትን ልናከብር የሚገባው ለምንድን ነው?

  • ለእነሱ እንደምንገዛ ማሳየት የምንችልባቸው አንዳንድ መንገዶች የትኞቹ ናቸው?

በጦርነት ወቅት አንዳንድ አገሮች፣ ሁለቱንም ወገኖች እየደገፉ ገለልተኛ እንደሆኑ ይናገራሉ። በእርግጥ ገለልተኛ መሆን ማለት ምን ማለት ነው? ዮሐንስ 17:16ን አንብቡ። ከዚያም ቪዲዮውን ተመልከቱና በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • ገለልተኛ መሆን ማለት ምን ማለት ነው?

ባለሥልጣናት ከአምላክ ሕግ ጋር የሚጋጭ ነገር እንድናደርግ ቢጠይቁንስ? የሐዋርያት ሥራ 5:28, 29ን አንብቡ። ከዚያም ቪዲዮውን ተመልከቱና በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • ሰዎች ያወጡት ሕግ ከአምላክ ሕግ ጋር በሚጋጭበት ጊዜ የትኛውን ሕግ ልንታዘዝ ይገባል?

  • ክርስቲያኖች ለባለሥልጣናት የማይታዘዙባቸውን አንዳንድ ሁኔታዎች መጥቀስ ትችላለህ?

4. በሐሳብም ሆነ በድርጊት ገለልተኛ ሁን

አንደኛ ዮሐንስ 5:21ን አንብቡ። ከዚያም ቪዲዮውን ተመልከቱና በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • በቪዲዮው ላይ አዬንጌ የፖለቲካ ፓርቲ አባል ላለመሆን እንዲሁም ለባንዲራ ሰላምታ እንደመስጠት ባሉ ብሔራዊ ሥነ ሥርዓቶች ላለመካፈል የወሰነው ለምንድን ነው?

  • ያደረገው ውሳኔ ትክክል ይመስልሃል?

የገለልተኝነት አቋማችንን ሊፈትኑ የሚችሉ ሌሎች ሁኔታዎች የትኞቹ ናቸው? ቪዲዮውን ተመልከቱ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • የተለያዩ አገሮች የሚሳተፉበትን ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ስንመለከት ገለልተኝነታችንን መጠበቅ የምንችለው እንዴት ነው?

  • ፖለቲከኞች የሚያደርጉት ውሳኔ እኛን የሚነካን በሚሆንበት ጊዜም እንኳ ገለልተኝነታችንን መጠበቅ የምንችለው እንዴት ነው?

  • የዜና ዘገባዎች ወይም አብረውን ጊዜ የሚያሳልፉ ሰዎች በገለልተኝነት አቋማችን ላይ ምን ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ?

ክርስቲያኖች በአስተሳሰብም ሆነ በድርጊት ገለልተኝነታቸውን መጠበቅ የሚኖርባቸው በየትኞቹ ሁኔታዎች ሥር ነው?

አንድ ሰው እንዲህ ብሎ ቢጠይቅህስ? “ለባንዲራ ሰላምታ የማትሰጠው ወይም ብሔራዊ መዝሙር የማትዘምረው ለምንድን ነው?”

  • ምን ብለህ ትመልሳለህ?

ማጠቃለያ

ክርስቲያኖች በሐሳባቸው፣ በንግግራቸውና በድርጊታቸው ከፖለቲካ ጉዳዮች ገለልተኛ ለመሆን ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ።

ክለሳ

  • ለመንግሥታት ምን የማድረግ ግዴታ አለብን?

  • ከፖለቲካ ጉዳዮች ገለልተኛ መሆን ያለብን ለምንድን ነው?

  • የገለልተኝነት አቋማችንን ሊፈትኑ የሚችሉ ሁኔታዎች የትኞቹ ናቸው?

ግብ

ምርምር አድርግ

የገለልተኝነት አቋማችንን ለመጠበቅ ስንል ምን መሥዋዕትነት መክፈል ሊያስፈልገን ይችላል?

ይሖዋ ፈጽሞ አላሳፈረንም (3:14)

ቤተሰቦች ገለልተኝነታቸውን ለሚፈትኑ ሁኔታዎች አስቀድመው መዘጋጀት የሚችሉት እንዴት ነው?

በሕዝባዊ ዝግጅቶች ወቅት የገለልተኝነት አቋማችንን መጠበቅ (4:25)

ለአገር ከመዋጋት በላይ ክብር የሚያስገኝ ነገር አለ የምንለው ለምንድን ነው?

“በአምላክ ዘንድ ሁሉ ነገር ይቻላል” (5:19)

ከሥራ ምርጫ ጋር የተያያዘ ውሳኔ ስታደርግ የዓለም ክፍል እንዳልሆንክ ማሳየት የምትችለው እንዴት ነው?

“እያንዳንዱ የራሱን ሸክም ሊሸከም ይገባዋል” (መጠበቂያ ግንብ መጋቢት 15, 2006)