በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ምዕራፍ 50

የቤተሰብህን ሕይወት አስደሳች ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?—ክፍል 2

የቤተሰብህን ሕይወት አስደሳች ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?—ክፍል 2

ልጆች የይሖዋ ስጦታዎች ናቸው። ይሖዋ፣ ወላጆች ስጦታ የሆኑትን ልጆቻቸውን በእንክብካቤ እንዲይዙ ይጠብቅባቸዋል። ደግሞም ወላጆችን በዚህ ረገድ ሊረዳቸው የሚችል ጠቃሚ ምክር ሰጥቷል። እሱ የሰጠው ምክር ልጆችም የቤተሰባቸው ሕይወት አስደሳች እንዲሆን ምን ማድረግ እንዳለባቸው ይጠቁማል።

1. ይሖዋ ለወላጆች ምን ምክር ሰጥቷል?

ይሖዋ፣ ወላጆች ልጆቻቸውን እንዲወዱና የቻሉትን ያህል ጊዜ ከእነሱ ጋር እንዲያሳልፉ ይጠብቅባቸዋል። በተጨማሪም ልጆቻቸውን ከጉዳት እንዲጠብቁ እንዲሁም የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች ተጠቅመው እንዲያሠለጥኗቸው ይፈልጋል። (ምሳሌ 1:8) አባቶችን ‘ልጆቻችሁን በይሖዋ ምክር አሳድጓቸው’ ብሏቸዋል። (ኤፌሶን 6:4⁠ን አንብብ።) ይሖዋ ወላጆች የእሱን መመሪያ ተከትለው ልጆቻቸውን ሲያሳድጉ ይደሰታል፤ ደግሞም ይህን ኃላፊነት ለሌላ ለማንም እንዲሰጡ አይፈልግም።

2. ይሖዋ ለልጆች ምን ምክር ሰጥቷል?

ይሖዋ ልጆችን “ለወላጆቻችሁ ታዘዙ” ብሏቸዋል። (ቆላስይስ 3:20⁠ን አንብብ።) ልጆች ወላጆቻቸውን የሚያከብሩና የሚታዘዙ ከሆነ ይሖዋንም ሆነ ወላጆቻቸውን ያስደስታሉ። (ምሳሌ 23:22-25) ኢየሱስ ልጅ ሳለ በዚህ ረገድ ጥሩ ምሳሌ ትቷል። ፍጹም የነበረ ቢሆንም ወላጆቹን ይታዘዛቸውና ያከብራቸው ነበር።—ሉቃስ 2:51, 52

3. በቤተሰብ ደረጃ ወደ ይሖዋ መቅረብ የምትችሉት እንዴት ነው?

ወላጅ ከሆንክ ልጆችህ ልክ እንደ አንተ ይሖዋን እንዲወዱ መርዳት እንደምትፈልግ ጥርጥር የለውም። ታዲያ ይህን ግብ ማሳካት የምትችለው እንዴት ነው? መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚከተለው በማለት የሰጠውን ምክር ተግባራዊ በማድረግ ነው፦ ‘የይሖዋን ትእዛዛት በልጆችህ ውስጥ ቅረጻቸው፤ በቤትህ ስትቀመጥና በመንገድ ላይ ስትሄድ ስለ እነሱ ተናገር።’ (ዘዳግም 6:7) “መቅረጽ” የሚለው ቃል አንድን ነገር ደጋግሞ በመናገር ማስተማርን ያመለክታል። ልጆች አንድን ነገር እንዲያስታውሱ ከተፈለገ ደጋግሞ መናገር እንደሚያስፈልግ ሳታስተውል አትቀርም። ይህ ጥቅስ ለልጆችህ ስለ ይሖዋ ደጋግመህ ለመናገር የሚያስችሉህን አጋጣሚዎች መፈለግ እንዳለብህ ይጠቁማል። በየሳምንቱ በቤተሰብ ለይሖዋ አምልኮ የምታቀርቡበት ጊዜ መመደባችሁ ጠቃሚ ነው። ልጆች ባይኖሩህም በየሳምንቱ የአምላክን ቃል የምታጠናበት ጊዜ መመደብህ ይጠቅምሃል።

ጠለቅ ያለ ጥናት

ሁሉም የቤተሰብ አባላት ደስተኛና ከስጋት ነፃ ሆነው እንዲኖሩ የሚረዱ ጠቃሚ ሐሳቦችን እንመለከታለን።

4. ልጆቻችሁን ፍቅር በሚንጸባረቅበት መንገድ አሠልጥኑ

ልጆችን ማሠልጠን ፈታኝ ሊሆን ይችላል። መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ረገድ ሊረዳን የሚችለው እንዴት ነው? ያዕቆብ 1:19, 20ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • ወላጆች ልጆቻቸውን በሚያነጋግሩበት ጊዜ ፍቅር ማሳየት የሚችሉት እንዴት ነው?

  • ወላጆች ተበሳጭተው እያለ ልጆቻቸውን መገሠጽ የሌለባቸው ለምንድን ነው? a

5. ልጆቻችሁን ከጥቃት ጠብቁ

ልጆቻችሁን ከጥቃት ለመጠበቅ ከእያንዳንዳቸው ጋር ስለ ፆታ ግንኙነት ማውራታችሁ አስፈላጊ ነው። እርግጥ ስለዚህ ጉዳይ ማውራት ሊያሳፍራችሁ ይችላል። ቪዲዮውን ተመልከቱ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • አንዳንድ ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ስለ ፆታ ግንኙነት ማውራት የሚከብዳቸው ለምንድን ነው?

  • አንዳንድ ወላጆች ልጆቻቸውን ስለ ፆታ ግንኙነት ለማስረዳት የትኛውን ዘዴ ተጠቅመዋል?

አስቀድሞ በትንቢት በተነገረው መሠረት የሰይጣን ዓለም ከጊዜ ወደ ጊዜ በክፋት እየጨመረ ነው። ሁለተኛ ጢሞቴዎስ 3:1, 13ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • በቁጥር 13 ላይ ከተገለጹት ክፉ ሰዎች መካከል አንዳንዶቹ በልጆች ላይ ፆታዊ ጥቃት ይፈጽማሉ። ከዚህ አንጻር ወላጆች ልጆቻቸውን ስለ ፆታ ግንኙነት ማስተማራቸውና እንዲህ ያለ ጥቃት ከሚፈጽሙ ሰዎች ራሳቸውን መጠበቅ የሚችሉት እንዴት እንደሆነ ማሠልጠናቸው አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

ይህን ታውቅ ነበር?

የይሖዋ ምሥክሮች ልጆችን ስለ ፆታ ግንኙነት ለማስተማርና ራሳቸውን ከጥቃት እንዲጠብቁ ለማሠልጠን የሚረዱ በርካታ መሣሪያዎችን አዘጋጅተዋል። የሚከተሉትን እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል፦

6. ወላጆችህን አክብር

ልጆችና በአሥራዎቹ ዕድሜ የሚገኙ ወጣቶች ወላጆቻቸውን የሚያነጋግሩበት መንገድ ለእነሱ አክብሮት እንዳላቸው የሚያሳይ ሊሆን ይገባል። ቪዲዮውን ተመልከቱ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • ልጆች ወላጆቻቸውን በአክብሮት ማነጋገራቸው አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

  • ልጆች ወላጆቻቸውን ሲያነጋግሩ ለእነሱ አክብሮት እንዳላቸው የሚያሳዩት እንዴት ነው?

ምሳሌ 1:8ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • ልጆች ወላጆቻቸው አንድ ነገር ሲያዟቸው ምን ማድረግ አለባቸው?

7. በቤተሰብ ደረጃ ለይሖዋ አምልኮ የምታቀርቡበት ጊዜ መድቡ

የይሖዋ ምሥክር የሆኑ ቤተሰቦች በየሳምንቱ ለይሖዋ አምልኮ የሚያቀርቡበት የተወሰነ ጊዜ ይመድባሉ። ይህን ጊዜ እንዴት ሊጠቀሙበት ይችላሉ? ቪዲዮውን ተመልከቱ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • አንድ ቤተሰብ፣ የቤተሰብ አምልኮ ፕሮግራሙን ቋሚ ማድረግ የሚችለው እንዴት ነው?

  • ወላጆች የቤተሰብ አምልኮ ፕሮግራማቸው ጠቃሚና አስደሳች እንዲሆን ምን ማድረግ ይችላሉ?—በዚህ ምዕራፍ መግቢያ ላይ ያለውን ፎቶግራፍ ተመልከት።

  • በቤተሰብ ደረጃ አንድ ላይ ማጥናት ተፈታታኝ እንዲሆንባችሁ የሚያደርገው ምን ሊሆን ይችላል?

ይሖዋ በጥንቷ እስራኤል የነበሩ ቤተሰቦች አዘውትረው በቃሉ ላይ እንዲወያዩ ይጠብቅባቸው ነበር። ዘዳግም 6:6, 7ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • በዚህ ጥቅስ ላይ ያለውን ምክር ተግባራዊ ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?

በቤተሰብ አምልኳችሁ ላይ ልታደርጉ የምትችሏቸው ነገሮች፦

  • ለጉባኤ ስብሰባ ተዘጋጁ።

  • የምትወዱትን የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ አንብባችሁ ተወያዩበት።

  • ትናንሽ ልጆች ካሏችሁ ከ​jw.org ላይ ለልጆች የወጡ መልመጃዎችን አውርዳችሁ ወይም አትማችሁ ተጠቀሙ።

  • በአሥራዎቹ ዕድሜ የሚገኙ ልጆች ካሏችሁ jw.org ላይ ለወጣቶች በወጡ ርዕሶች ላይ ተወያዩ።

  • በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኝን አንድ ታሪክ ተጠቅማችሁ ከልጆቻችሁ ጋር ድራማ ሥሩ።

  • jw.org ላይ ያለ አንድ ቪዲዮ አይታችሁ ተወያዩበት።

አንዳንዶች እንዲህ ይላሉ፦ “የመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳብ ከባድ ስለሆነ ልጆች ሊረዱት አይችሉም።”

  • አንተ ምን ትላለህ?

ማጠቃለያ

ይሖዋ ወላጆች ልጆቻቸውን እንዲወዱ፣ እንዲያሠለጥኑና ከጥቃት እንዲጠብቁ ይፈልጋል፤ በተጨማሪም ልጆች ወላጆቻቸውን እንዲያከብሩና እንዲታዘዙ፣ ቤተሰቦች ደግሞ በአንድነት ለእሱ አምልኮ እንዲያቀርቡ ይጠብቅባቸዋል።

ክለሳ

  • ወላጆች ልጆቻቸውን ማሠልጠንና ከጥቃት መጠበቅ የሚችሉት እንዴት ነው?

  • ልጆች ወላጆቻቸውን እንደሚያከብሩ ማሳየት የሚችሉት እንዴት ነው?

  • በቤተሰብ ደረጃ ለይሖዋ አምልኮ ለማቅረብ በየሳምንቱ የተወሰነ ጊዜ መመደብ ምን ጥቅም አለው?

ግብ

ምርምር አድርግ

ልጆችን አዋቂ ሲሆኑ ለሚጠብቃቸው ሕይወት ለማዘጋጀት የትኞቹን ትምህርቶች ልታስተምሯቸው ይገባል?

“ልጆች ሊማሯቸው የሚገቡ ስድስት ትምህርቶች” (ንቁ! ቁጥር 2 2019)

መጽሐፍ ቅዱስ አረጋውያን ወላጆቻቸውን ለሚንከባከቡ ሰዎች ምን ጠቃሚ ምክር ይሰጣል?

“መጽሐፍ ቅዱስ አረጋውያን ወላጆችን መጦርን በተመለከተ ምን ይናገራል?” (ድረ ገጻችን ላይ የወጣ ርዕስ)

ልጆቹን እንዴት ማሳደግ እንዳለበት ግራ ተጋብቶ የነበረ አንድ ሰው በዚህ ረገድ እንዲሳካለት የረዳው ምንድን ነው?

ይሖዋ ልጆቻችንን እንዴት እንደምናሳድግ አስተምሮናል (5:58)

አባቶች ከወንዶች ልጆቻቸው ጋር ይበልጥ መቀራረብ የሚችሉት እንዴት ነው?

“ከወንድ ልጅህ ጋር ያለህ ጓደኝነት እንዲቀጥል ምን ማድረግ ትችላለህ?” (መጠበቂያ ግንብ ኅዳር 1, 2011)

a በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ተግሣጽ” የሚለው ቃል ትምህርት፣ መመሪያና እርማት ከመስጠት ጋር የተያያዘ ነው። በልጆች ላይ ጉዳት ማድረስን ወይም በጭካኔ መቅጣትን አያመለክትም።—ምሳሌ 4:1