በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ምዕራፍ 54

“ታማኝና ልባም ባሪያ” የሚጫወተው ሚና

“ታማኝና ልባም ባሪያ” የሚጫወተው ሚና

ኢየሱስ የክርስቲያን ጉባኤ ራስ ነው። (ኤፌሶን 5:23) በዛሬው ጊዜ ‘በታማኝና ልባም ባሪያ’ አማካኝነት በምድር ላይ ያሉ ተከታዮቹን ከሰማይ ሆኖ ይመራል። (ማቴዎስ 24:45⁠ን አንብብ።) ይህ “ባሪያ” በራሱ በኢየሱስ የተሾመ እንደመሆኑ መጠን የተወሰነ ሥልጣን አለው፤ ያም ሆኖ የክርስቶስ ባሪያ በመሆን የጌታን ወንድሞች ማገልገሉን ይቀጥላል። ለመሆኑ “ታማኝና ልባም ባሪያ” ማን ነው? እኛን የሚንከባከበንስ እንዴት ነው?

1. “ታማኝና ልባም ባሪያ” ማን ነው?

ከጥንት ጊዜ አንስቶ ይሖዋ ሕዝቡን ለመምራት አንድን ሰው ወይም የተወሰኑ ሰዎችን ያቀፈን አነስተኛ ቡድን ሲጠቀም ቆይቷል። (ሚልክያስ 2:7፤ ዕብራውያን 1:1) ኢየሱስ ከሞተ በኋላ በኢየሩሳሌም ያሉ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች አመራር መስጠት ጀመሩ። (የሐዋርያት ሥራ 15:2) ይህንኑ አሠራር በመከተል በዛሬው ጊዜም የተወሰኑ ሽማግሌዎችን ያቀፈ አንድ አነስተኛ ቡድን ማለትም የይሖዋ ምሥክሮች የበላይ አካል መንፈሳዊ ምግብ ያቀርባል፤ እንዲሁም የስብከቱን ሥራ ይመራል። ይህ ቡድን ‘ኢየሱስ የሾመው ታማኝና ልባም ባሪያ’ ነው። (ማቴዎስ 24:45ለ) ሁሉም የበላይ አካል አባላት በመንፈስ የተቀቡ ክርስቲያኖች ሲሆኑ ምድራዊ ሕይወታቸው ካበቃ በኋላ ከክርስቶስ ጋር በሰማይ ለመግዛት በተስፋ ይጠባበቃሉ።

2. ታማኙ ባሪያ ምን ዓይነት መንፈሳዊ ምግብ ያቀርባል?

ኢየሱስ ታማኙ ባሪያ ለክርስቲያኖች ‘በተገቢው ጊዜ ምግባቸውን እንደሚሰጥ’ ተናግሯል። (ማቴዎስ 24:45ሀ) የምንበላው ምግብ ሰውነታችን ጠንካራና ጤናማ እንዲሆን ይረዳናል፤ በተመሳሳይም መንፈሳዊ ምግብ ማለትም በአምላክ ቃል ውስጥ የሚገኘው ትምህርት ለይሖዋ ታማኝ ሆነን ለመቀጠልና ኢየሱስ የሰጠንን ሥራ ለማከናወን የሚያስፈልገንን ብርታት ይሰጠናል። (1 ጢሞቴዎስ 4:6) ይህን መንፈሳዊ ምግብ የምናገኘው በጉባኤ ስብሰባዎች፣ በትላልቅ ስብሰባዎች እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስ ላይ በተመሠረቱ ጽሑፎችና ቪዲዮዎች አማካኝነት ሲሆን የአምላክን ፈቃድ ለማወቅ ብሎም ከእሱ ጋር ያለንን ወዳጅነት ለማጠናከር ይረዳናል።

ጠለቅ ያለ ጥናት

“ታማኝና ልባም ባሪያ” ማለትም የበላይ አካሉ የሚያስፈልገን ለምን እንደሆነ እንመለከታለን።

የበላይ አካሉ በዓለም ዙሪያ ላሉ የይሖዋ ምሥክሮች መንፈሳዊ ምግብ ያቀርባል፣ አመራር ይሰጣል እንዲሁም አስፈላጊውን እርዳታ ያደርጋል

3. የይሖዋ ሕዝቦች የተደራጁ መሆን አለባቸው

የበላይ አካሉ በኢየሱስ አመራር ሥር ሆኖ የይሖዋ ምሥክሮችን ሥራ ያደራጃል። የጥንቶቹ ክርስቲያኖችም ተመሳሳይ አሠራር ይከተሉ ነበር። ቪዲዮውን ተመልከቱ

አንደኛ ቆሮንቶስ 14:33, 40ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • ይህ ጥቅስ ይሖዋ፣ ምሥክሮቹ የተደራጁ እንዲሆኑ እንደሚፈልግ የሚያሳየው እንዴት ነው?

4. ታማኙ ባሪያ የስብከቱ ሥራችንን ያደራጃል

የጥንቶቹ ክርስቲያኖች ለስብከቱ ሥራ ከሁሉ የላቀ ቦታ ይሰጡ ነበር። የሐዋርያት ሥራ 8:14, 25ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • ከጥንቶቹ ክርስቲያኖች መካከል ለስብከቱ ሥራ አመራር ይሰጡ የነበሩት እነማን ናቸው?

  • ጴጥሮስና ዮሐንስ ሌሎቹ ሐዋርያት ለሰጧቸው መመሪያ ምን ምላሽ ሰጥተዋል?

የበላይ አካሉ ለስብከቱ ሥራ ትልቅ ቦታ ይሰጣል። ቪዲዮውን ተመልከቱ

ኢየሱስ የስብከቱ ሥራ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ተናግሯል። ማርቆስ 13:10ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • የበላይ አካሉ ለስብከቱ ሥራ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ለምንድን ነው?

  • ይህን ዓለም አቀፋዊ ሥራ ለማደራጀት “ታማኝና ልባም ባሪያ” የሚያስፈልገው ለምንድን ነው?

5. ታማኙ ባሪያ አመራር ይሰጣል

የበላይ አካሉ በዓለም ዙሪያ ላሉ ክርስቲያኖች አመራር ይሰጣል። አመራር የሚሰጠው በምን ላይ ተመሥርቶ ነው? በጥንቶቹ ክርስቲያኖች ዘመን የነበረውን የበላይ አካል እንደ ምሳሌ እንመልከት። የሐዋርያት ሥራ 15:1, 2ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • በጥንት ዘመን በነበሩ አንዳንድ ክርስቲያኖች መካከል ምን ውዝግብ ተነስቶ ነበር?

  • ጳውሎስ፣ በርናባስና ሌሎች ወንድሞች ለጉዳዩ መፍትሔ ለማግኘት ምን አደረጉ?

የሐዋርያት ሥራ 15:12-18, 23-29ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • የበላይ አካሉ ውሳኔ ከማድረጉ በፊት የአምላክን አመራር ለማግኘት ምን አደረገ?—ቁጥር 12, 15 እና 28⁠ን ተመልከት።

የሐዋርያት ሥራ 15:30, 31ን እንዲሁም 16:4, 5ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • የጥንቶቹ ክርስቲያኖች ለበላይ አካሉ መመሪያ ምን ምላሽ ሰጡ?

  • ታዛዥ በመሆናቸው ይሖዋ የባረካቸው እንዴት ነው?

ሁለተኛ ጢሞቴዎስ 3:16ን እና ያዕቆብ 1:5ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • በዛሬው ጊዜ የበላይ አካሉ ውሳኔ የሚያደርገው እንዴት ነው?

አንዳንዶች እንዲህ ይላሉ፦ “በበላይ አካሉ መመራት ማለት የሰው ተከታይ መሆን ማለት ነው።”

  • የበላይ አካሉን የሚመራው ኢየሱስ ነው ብለህ እንድታምን የሚያደርግህ ምንድን ነው?

ማጠቃለያ

በክርስቶስ የተሾመው “ታማኝና ልባም ባሪያ” የበላይ አካሉ ነው። በዓለም ዙሪያ ላሉ ክርስቲያኖች አመራር ይሰጣል እንዲሁም መንፈሳዊ ምግብ ያቀርባል።

ክለሳ

  • ‘ታማኝና ልባም ባሪያን’ የሾመው ማን ነው?

  • የበላይ አካሉ እኛን የሚንከባከበን እንዴት ነው?

  • በክርስቶስ የተሾመው “ታማኝና ልባም ባሪያ” የበላይ አካሉ እንደሆነ ታምናለህ?

ግብ

ምርምር አድርግ

የበላይ አካሉ እምነት የሚጣልበት መንፈሳዊ ምግብ እንድናገኝ የሚያደርገው እንዴት ነው?

ትክክለኛ መረጃ የያዙ ጽሑፎችን ማዘጋጀት (17:18)

የበላይ አካል አባላት ኢየሱስ ለሰጣቸው ሥራ ምን አመለካከት አላቸው?

ውድ መብት (7:04)

የጉባኤ ስብሰባዎቻችንና ትላልቅ ስብሰባዎቻችን ይሖዋ የበላይ አካሉን እየመራው እንዳለ የሚያሳዩት እንዴት ነው?

ይሖዋ ሕዝቡን ያስተምራል (9:39)