በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ምዕራፍ 60

እድገት ማድረግህን ቀጥል

እድገት ማድረግህን ቀጥል

በዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ፕሮግራም አማካኝነት ስለ ይሖዋ ብዙ ነገር ተምረሃል። የተማርከው ነገር ለእሱ ጥልቅ ፍቅር እንድታዳብር ብሎም ራስህን ወስነህ እንድትጠመቅ አነሳስቶህ ሊሆን ይችላል። አሊያም ደግሞ በቅርቡ እንዲህ ያለ እርምጃ ለመውሰድ እያሰብክ ይሆናል። ይሁንና ተጠመቅክ ማለት ከዚያ በኋላ ማድረግ የሚያስፈልግህ ነገር የለም ማለት አይደለም። ወደ ይሖዋ ለመቅረብ የምታደርገው ጥረት ለዘላለም የሚቀጥል ሊሆን ይገባል። ይህን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?

1. ከይሖዋ ጋር ያለህን ወዳጅነት ማጠናከርህን መቀጠል ያለብህ ለምንድን ነው?

ከይሖዋ ጋር ያለን ወዳጅነት እየተጠናከረ እንዲሄድ ከፍተኛ ጥረት ማድረግ አለብን። እንዲህ ማድረጋችን ከእሱ “ቀስ በቀስ እንዳንወሰድ” ይረዳናል። (ዕብራውያን 2:1) ታዲያ ይሖዋን በታማኝነት ማገልገላችንን ለመቀጠል ምን ማድረግ እንችላለን? በስብከቱ ሥራ ራሳችንን ማስጠመዳችን እንዲሁም አምላካችንን ይበልጥ ማገልገል የምንችልባቸውን ሌሎች መንገዶች መፈለጋችን ጠቃሚ ነው። (ፊልጵስዩስ 3:16⁠ን አንብብ።) ይሖዋን ማገልገል ከሁሉ የተሻለ ሕይወት እንዲኖረን ይረዳናል!—መዝሙር 84:10

2. በቀጣይነት ልታደርግ የሚገባህ ሌላው ነገር ምንድን ነው?

መጽሐፍ ቅዱስን የምትማርበት ይህ ፕሮግራም እዚህ ላይ ቢደመደምም ከክርስቲያኖች የሚጠበቁትን ነገሮች ማድረግህን መቀጠል ይኖርብሃል። መጽሐፍ ቅዱስ “አዲሱን ስብዕና መልበስ” እንደሚኖርብን ይናገራል። (ኤፌሶን 4:23, 24) የአምላክን ቃል ማጥናትህን እንዲሁም በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ መገኘትህን ስትቀጥል ስለ ይሖዋና ስለ ባሕርያቱ አዳዲስ ነገሮችን መማርህ አይቀርም። በሕይወትህ ውስጥ ይሖዋን ይበልጥ መምሰል የምትችልባቸውን መንገዶች ለማስተዋል ሞክር። በተጨማሪም እሱን ለማስደሰት ስትል አስፈላጊውን ለውጥ ማድረግህን ቀጥል።

3. ይሖዋ እድገት እንድታደርግ የሚረዳህ እንዴት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ “አምላክ . . . ራሱ ሥልጠናችሁ እንዲጠናቀቅ ያደርጋል። ጽኑ እንድትሆኑ ያደርጋችኋል፤ ደግሞም ያጠነክራችኋል፤ አጽንቶም ያቆማችኋል።” (1 ጴጥሮስ 5:10) ሁላችንም የተሳሳተ ነገር ለማድረግ የምንፈተንበት ጊዜ አለ። ሆኖም ይሖዋ የሚያጋጥሙንን ፈተናዎች ለመቋቋም የሚያስችል ብርታት ይሰጠናል። (መዝሙር 139:23, 24) እሱን በታማኝነት ለማገልገል የሚያነሳሳ ፍላጎትም ሆነ እንዲህ ለማድረግ የሚያስችል ኃይል እንደሚሰጥህ ቃል ገብቷል።—ፊልጵስዩስ 2:13⁠ን አንብብ።

ጠለቅ ያለ ጥናት

እድገት ማድረግህን መቀጠል የምትችለው እንዴት እንደሆነና ይሖዋ የሚባርክህ እንዴት እንደሆነ እንመለከታለን።

4. ከቅርብ ወዳጅህ ጋር የሐሳብ ልውውጥ ማድረግህን ቀጥል

መጸለይህና መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናትህ የይሖዋ ወዳጅ ለመሆን ረድቶሃል። እነዚህን ነገሮች ማድረግህን መቀጠልህ ወደ እሱ ይበልጥ እንድትቀርብ የሚረዳህ እንዴት ነው?

መዝሙር 62:8ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • ከይሖዋ ጋር የመሠረትከውን ወዳጅነት ለማጠናከር ወደ እሱ የምታቀርበውን ጸሎት ማሻሻል የምትችለው እንዴት ነው?

መዝሙር 1:2ን እና የግርጌ ማስታወሻውን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • ከይሖዋ ጋር የመሠረትከውን ወዳጅነት ለማጠናከር የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብህን ማሻሻል የምትችለው እንዴት ነው?

ከግል ጥናትህ የተሟላ ጥቅም ማግኘት የምትችለው እንዴት ነው? አንዳንድ ጠቃሚ ሐሳቦችን ለማየት ቪዲዮውን ተመልከቱ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • በቪዲዮው ላይ ከተጠቀሱት ጠቃሚ ሐሳቦች መካከል የትኞቹን ተግባራዊ ማድረግ ትችላለህ?

  • ስለ የትኞቹ ጉዳዮች ማጥናት ትፈልጋለህ?

5. መንፈሳዊ ግቦች አውጣ

መንፈሳዊ ግቦች ማውጣትህ እድገት ማድረግህን እንድትቀጥል ይረዳሃል። ቪዲዮውን ተመልከቱ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • በቪዲዮው ላይ ካሜሮን መንፈሳዊ ግቦችን በማውጣቷ ምን ጥቅም አግኝታለች?

አብዛኞቻችን ወደ ሌላ አገር ተዛውረን ለመስበክ ሁኔታችን አይፈቅድልን ይሆናል። ሆኖም ሁላችንም ልንደርስባቸው የምንችላቸውን ግቦች ልናወጣ እንችላለን። ምሳሌ 21:5ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • ከጉባኤህ ጋር በተያያዘ ምን ግብ ልታወጣ ትችላለህ?

  • ከመስክ አገልግሎት ጋር በተያያዘ ምን ግብ ልታወጣ ትችላለህ?

በዚህ ጥቅስ ላይ የተሰጠው ምክር ግብህ ላይ ለመድረስ የሚረዳህ እንዴት ነው?

ልታወጣቸው የምትችላቸው ግቦች

  • ወደ ይሖዋ የምታቀርበውን ጸሎት ማሻሻል

  • ሙሉውን መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብ

  • በጉባኤህ ውስጥ ካሉ ሰዎች ሁሉ ጋር መተዋወቅ

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማስጀመር

  • ረዳት አቅኚ ወይም የዘወትር አቅኚ ሆኖ ማገልገል

  • ወንድም ከሆንክ የጉባኤ አገልጋይ ለመሆን የሚያስፈልገውን ብቃት ማሟላት

6. ለዘላለም በደስታ ኑር!

መዝሙር 22:26ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • አሁንም ሆነ ለዘላለም በደስታ ለመኖር ምን ማድረግ ይኖርብሃል?

ማጠቃለያ

ከይሖዋ ጋር ያለህን ወዳጅነት ማጠናከርህንና መንፈሳዊ ግቦች ማውጣትህን ቀጥል። እንዲህ የምታደርግ ከሆነ ለዘላለም በደስታ መኖር ትችላለህ!

ክለሳ

  • ይሖዋ በታማኝነት እንድታገለግለው እንደሚረዳህ እርግጠኛ መሆን የምትችለው ለምንድን ነው?

  • ከይሖዋ ጋር ያለህን ወዳጅነት ማጠናከር የምትችለው እንዴት ነው?

  • መንፈሳዊ ግቦችን ማውጣትህ እድገት ለማድረግ የሚረዳህ እንዴት ነው?

የረጅም ጊዜ ግብ

ምርምር አድርግ

ይሖዋ የበለጠ ቦታ የሚሰጠው ለእሱ ያለንን ታማኝነት ለሚያሳይ አንድ የሚያስደምም ድርጊት ነው ወይስ በሕይወት ዘመናችን ሁሉ ለምናሳየው ታማኝነት?

እንደ አብርሃም ታማኞች ሁኑ (9:20)

ታማኝ የሆኑ የይሖዋ አገልጋዮችም እንኳ ደስታቸውን የሚያጡበት ጊዜ ይኖራል። እንዲህ ያለ ሁኔታ ሲያጋጥመን ደስታችንን መልሰን ማግኘት የምንችለው እንዴት ነው?

ጥናትና ማሰላሰል ደስታን መልሶ ለማግኘት ይረዳል (5:25)

መንፈሳዊ ግቦች ማውጣትና ግቦችህ ላይ መድረስ የምትችለው እንዴት ነው?

“ፈጣሪህን ለማክበር መንፈሳዊ ግቦች አውጣ” (መጠበቂያ ግንብ ሐምሌ 15, 2004)

መንፈሳዊ ጉልምስና አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? መንፈሳዊ ጉልምስና ላይ መድረስ የሚቻለውስ እንዴት ነው?

“‘ታላቁ የይሖዋ ቀን ቀርቧል’—ወደ ጉልምስና ግፉ” (መጠበቂያ ግንብ ግንቦት 15, 2009)